+ -

عَنْ حُذَيْفَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَا تَقُولُوا: مَا شَاءَ اللهُ وَشَاءَ فُلَانٌ، وَلَكِنْ قُولُوا: مَا شَاءَ اللهُ ثُمَّ شَاءَ فُلَانٌ».

[صحيح بمجموع طرقه] - [رواه أبو داود والنسائي في الكبرى وأحمد] - [السنن الكبرى للنسائي: 10755]
المزيــد ...

ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ከሻ (ከፈለገ) እና እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' አትበሉ። ይልቁንም 'አላህ ከሻ (ከፈለገ) ከዚያም እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' በሉ።"

[ከሁሉም ሰነዶቹ አንፃር ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ነሳኢ በኩብራ ውስጥ፣ አሕመድ ዘግበውታል።] - [አስሱነኑል ኩብራ ነሳኢ - 10755]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማንኛውንም ሙስሊም በንግግሩ "አላህ ከሻ (ከፈለገ) እና እከሌ ከሻ (ከፈለገ)" ከማለት ከለከሉ። ወይም "አላህና እከሌ ሽተውት (ፈልገውት)" ከማለት ከለከሉ። ይህም የሆነው የአላህ መሻትና ፍላጎት ልቅ በመሆኑ አንድም የሚጋራው ስለሌለ ነው። "እና" የምትለውን ቃል በአጣማሪነት መጠቀማችን በመሻት በኩል ከአላህ ጋር የሚጋራ ሌላ አካል እንዳለና በመካከላቸው ያለው መሻትም እኩል እንደሆነ ይጠቁማል። ነገር ግን "አላህ ሽቶት ከዚያም እከሌ ሽቶታል።" ይበል። "ከዚያም" የሚለውን ቃል "እና" በሚለው ተለዋጭ አድርጎ በመጠቀም የባሪያን መሻት የአላህን መሻት ተከትሎ የሚመጣ መሆኑን ግልፅ ያድርግ። ምክንያቱም "ከዚያም" የምትለው ቃል ቅደም ተከተልን ትጠቁማለችና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. "አላህና አንተ ሽታቹሀል።" ማለትና ይህን የመሳሰሉ ቃላቶችን በ "እና" አጣምሮ አሏህ ጋር መጠቀም የቃላትና የንግግር ሺርክ ስለሆነ ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
  2. "አላህ ሽቶታል ከዚያም አንተ ሽተኸዋል" የሚለው ንግግርና ይህን የመሳሰሉ "ከዚያም" በሚለው መስተፃምር አሏህ ጋር መጠቀም የተከለከለው ነገር ስለሚወገድ ይፈቀዳል።
  3. ለአላህ መሻት እንደምናፀድቅለት፣ ለባሪያም መሻት እንደምናፀድቅለት እና የባሪያ መሻት የአላህን መሻት ተከትሎ የሚመጣ መሆኑን እንረዳለን።
  4. በቃል ደረጃ እንኳ ቢሆን በአላህ መሻት ላይ ፍጡራንን ማጋራት መከልከሉን እንረዳለን።
  5. ተናጋሪው የባሪያ መሻት እንደ አላህ መሻት ነው፤ ከአላህ መሻት ጋር በአካታችነትም ይሁን በስፋት እኩል ነው ብሎ ካመነ ወይም ባሪያ ራሱን የቻለ (አላህ ባይሻለትም) የመሻት አቅም አለው ብሎ ካመነ ትልቁ ሺርክ ይሆናል። ከአላህ በታች የሆነ መሻት ነው ያለው ብሎ ካመነ ግን ትንሹ ሺርክ ይሆናል።
ተጨማሪ