عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«حَقُّ الْمُسْلِمِ عَلَى الْمُسْلِمِ سِتٌّ» قِيلَ: مَا هُنَّ يَا رَسُولَ اللهِ؟، قَالَ: «إِذَا لَقِيتَهُ فَسَلِّمْ عَلَيْهِ، وَإِذَا دَعَاكَ فَأَجِبْهُ، وَإِذَا اسْتَنْصَحَكَ فَانْصَحْ لَهُ، وَإِذَا عَطَسَ فَحَمِدَ اللهَ فَسَمِّتْهُ، وَإِذَا مَرِضَ فَعُدْهُ وَإِذَا مَاتَ فَاتَّبِعْهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2162]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
«"አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ያሉት መብቶች ስድስት ናቸው።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምንድን ናቸው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ያገኘኸው ጊዜ ሰላምታን አቅርብለት፤ የጠራህ ጊዜ ጥሪውን አክብር፤ ካንተ ምክርን በፈለገ ጊዜ ምከረው፤ አስነጥሶ አላህን ያመሰገነ ጊዜ "የርሐሙከሏህ" በለው፤ የታመመ ጊዜ ጠይቀው፤ የሞተም ጊዜ ቅበረው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2162]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ወንድሙ ላይ ካሉት ሐቆች መካከል ስድስቱን ጠቀሱ፡ የመጀመሪያው: ባገኘው ጊዜ "አስሰላሙ ዐለይኩም" (ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን) በማለት ሰላምታውን ያቅርብለት። እርሱም "ወዐለይኩሙ-ስሰላም" በማለት ሰላምታውን ይመልስለት። ሁለተኛው: ለሰርግና ለሌሎች ድግሶች በጠራው ጊዜ ጥሪውን ማክበር ነው። ሶስተኛው: ምክር ባስፈለገው ጊዜ ያለምንም ማሞኘትና ማታለል መምከር ነው። አራተኛው: አስነጥሶ "አልሐምዱሊላህ" (ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባው ነው) ያለ ጊዜ "የርሐሙከላህ" (አላህ ይዘንልህ፤ ይቅር ይበልህ) በማለት አስደስተው። እርሱም "የህዲኩሙሏህ ወዩስሊሕ ባለኩም" (አላህ ይምራህ፤ ጉዳይህንም ያስተካክልልህ) በማለት ይመልስ። አምስተኛው: በታመመ ጊዜ ይጠይቀው፤ ይጎብኘው። ስድስተኛው: በሞተ ጊዜ ይስገድበት፤ እስኪቀበር ድረስም ጀናዛውን ይከተለው።