عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«انْظُرُوا إِلَى مَنْ أَسْفَلَ مِنْكُمْ، وَلَا تَنْظُرُوا إِلَى مَنْ هُوَ فَوْقَكُمْ، فَهُوَ أَجْدَرُ أَلَّا تَزْدَرُوا نِعْمَةَ اللهِ عَلَيْكُمْ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2963]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ከናንተ በታች ወዳለ ሰው ተመልከቱ እንጂ ከናንተ በላይ ወዳለ ሰው አትመልከቱ! ይህን ማድረጋችሁ (የበታቻችሁን ማየት) አላህ በናንተ ላይ የዋለውን ፀጋ አሳንሶ ከማየት ይታደጋችኃል።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2963]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሙስሊም የሆነ ሰው በዱንያ ጉዳዮቹ፣ በማዕረግ፣ በገንዘብ፣ በክብርና በሌሎችም ነገሮች በአንፃራዊ ሁኔታው ዝቅ ወዳለ ሰው እንዲመለከትና በዱንያዊ ጉዳዮች ደሞ ከርሱ የበላዩና በዱኒያ የሚበልጠው ወደሆነ ሰው እንዳይመለከት አዘዙ። ከርሱ በታች ወደሆነ ሰው መመልከት አላህ የዋለልህን ፀጋ እንዳታሳንስና ዝቅ እንዳታደርግ የሚያግዝ ነው።