عَنْ أَبِي ذَرٍّ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«يَا أَبَا ذَرٍّ إِذَا طَبَخْتَ مَرَقَةً فَأَكْثِرْ مَاءَهَا، وَتَعَاهَدْ جِيرَانَكَ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2625]
المزيــد ...
ከአቡ ዘር ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል:
"አቡ ዘር ሆይ! መረቅ የቀቀልክ ጊዜ ውሃውን አብዛ! ጎረቤቶችህንም ተከታተል።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2625]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አቡ ዘር አልጚፋሪይን ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - መረቅ የቀቀለ ጊዜ ውሃውንና መረቁን እንዲያበዛና ከመረቁ ለጎረቤቶቹ በመላክም እንዲከታተላቸው አነሳሱት።