عَنْ أَبِي شُرَيْحٍ رضي الله عنه أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«وَاللَّهِ لاَ يُؤْمِنُ، وَاللَّهِ لاَ يُؤْمِنُ، وَاللَّهِ لاَ يُؤْمِنُ»، قِيلَ: وَمَنْ يَا رَسُولَ اللَّهِ؟ قَالَ: «الَّذِي لاَ يَأْمَنُ جَارُهُ بَوَايِقَهُ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6016]
المزيــد ...
ከአቡ ሹረይሕ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ፦
«"ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም!" "የአላህ መልክተኛ ሆይ ማን ነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ጎረቤቱ ተንኮሉን ያላመነው ሰው ነው።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6016]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ማሉ። መሃላቸውንም ሶስት ጊዜ አድርገው አፅንዖት ሰጥተው እንዲህ አሉ: "ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም!" አሉ። ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን ነው ያላመነው?" አሉ። እርሳቸውም "ከክዳቱ፣ ከግፉና ከክፋቱ አንፃር ጎረቤቱ የሚፈራው ነው።" አሉ።