+ -

عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: مَا خَطَبَنَا نَبِيُّ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِلَّا قَالَ:
«لَا إِيمَانَ لِمَنْ لَا أَمَانَةَ لَهُ، وَلَا دِينَ لِمَنْ لَا عَهْدَ لَهُ».

[حسن لغيره] - [رواه أحمد] - [مسند أحمد: 12383]
المزيــد ...

ከአነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ ነቢይ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሳይሉን አንድም ኹጥባ አያደርጉም ነበር:
"አማና (አደራ) የሌለው ሰው ኢማን የለውም፤ ቃልኪዳን የማያከብር የሆነ ሰው ሃይማኖት የለውም።"»

[Hasan/Sound by virtue of corroborating evidence] - [አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሙስነድ አሕመድ - 12383]

ትንታኔ

አነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለው ተናገሩ: ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ኹጥባ ሲያደርጉ ወይም ሲመክሩ ሁለት ነገሮችን ሳይጠቅሱ የሚያልፉበት ጊዜ በጣም ጥቂት ጊዜያት ነው። የመጀመሪያው: አንድን አካል በገንዘብ ወይም በነፍስ ወይም በቤተሰብ ጉዳይ ነፍሱ ውስጥ ከዳተኝነት ያለችበት ሰው የተሟላ ኢማን የለውም። ሁለተኛው: ቃልኪዳንን የሚያፈርስ ሰው የተሟላ ሃይማኖት የለውም።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አደራን በመወጣት ላይና ቃልኪዳንን በመሙላት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። እነዚህን ሁለት ነገሮች ማፍረስ ኢማንን ያፈርሳል።
  2. አደራን ከመካድና ቃልኪዳንን ከማፍረስ መከልከሉንና እነዚህን መፈፀምም ከትላልቅ ወንጀሎች እንደሆነ እንረዳለን።
  3. ሐዲሡ በአላህና በባሪያው መካከል ያለንም ይሁን ፍጡራን እርስ በርሳቸው መካከል ያለውንም አደራ መጠበቅንና ቃልኪዳን ማክበርን ያካትታል።
ትርጉም: እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ሲንሃላዊ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ