+ -

عن ابْنِ عُمَرَ رَضيَ اللهُ عنهُما قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«أَيُّمَا امْرِئٍ قَالَ لِأَخِيهِ: يَا كَافِرُ، فَقَدْ بَاءَ بِهَا أَحَدُهُمَا، إِنْ كَانَ كَمَا قَالَ، وَإِلَّا رَجَعَتْ عَلَيْهِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 60]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ:
"ማንኛውም ለወንድሙ ‹አንተ ከሀዲ› ያለ ሰው በርግጥም በርሷ (በከሀዲነቷ) ላይ አንዳቸው ወድቀዋል። እንዳለው ሆኖ ከሆነ (መልካም) ያለበለዚያ ወደርሱ ትመለሳለች።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 60]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አንድ ሙስሊም ለሙስሊም ወንድሙ "አንተ ካፊር" እንዳይል አስጠነቀቁ። የከሀዲነት ቃሏንም በርግጥ አንዳቸው ይገባቸዋል። ሰውዬው እንዳለው በትክክል ከሀዲ ሆኖ ከሆነ መልካም ያለበለዚያ ግን ክህደቱ ወንድሙን ከሀዲ ወዳለው ተናጋሪ ይመለሳል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ኢንዶኔዥያኛ ቬትናማዊ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አንድ ሙስሊም ሙስሊም ወንድሙ ላይ የሌለበትን የአመፅና ክህደት መገለጫ ከመለጠፍ መከልከሉን እንረዳለን።
  2. ከዚህ መጥፎ ንግግር መከልከሉንና ተናጋሪው እንደዛ ያለው ሙስሊም ወንድሙን ከሆነ ትልቅ አደጋ ላይ እንደወደቀ እንረዳለን። ምላስን መጠበቅና በእውቀት ላይ ተመስርቶ ካልሆነ በቀር አለመናገር እንደሚገባም እንረዳለን።
ተጨማሪ