عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ:
قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لِمُعَاذِ بْنِ جَبَلٍ، حِينَ بَعَثَهُ إِلَى الْيَمَنِ: «إِنَّكَ سَتَأْتِي قَوْمًا أَهْلَ كِتَابٍ، فَإِذَا جِئْتَهُمْ فَادْعُهُمْ إِلَى أَنْ يَشْهَدُوا أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، فَإِنْ هُمْ أَطَاعُوا لَكَ بِذَلِكَ، فَأَخْبِرْهُمْ أَنَّ اللهَ قَدْ فَرَضَ عَلَيْهِمْ خَمْسَ صَلَوَاتٍ فِي كُلِّ يَوْمٍ وَلَيْلَةٍ، فَإِنْ هُمْ أَطَاعُوا لَكَ بِذَلِكَ، فَأَخْبِرْهُمْ أَنَّ اللهَ قَدْ فَرَضَ عَلَيْهِمْ صَدَقَةً تُؤْخَذُ مِنْ أَغْنِيَائِهِمْ فَتُرَدُّ عَلَى فُقَرَائِهِمْ، فَإِنْ هُمْ أَطَاعُوا لَكَ بِذَلِكَ، فَإِيَّاكَ وَكَرَائِمَ أَمْوَالِهِمْ، وَاتَّقِ دَعْوَةَ الْمَظْلُومِ، فَإِنَّهُ لَيْسَ بَيْنَهُ وَبَيْنَ اللهِ حِجَابٌ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1496]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል፡
"የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙዐዝ ቢን ጀበልን ወደ የመን በሚልኩበት ጊዜ እንዲህ አሉት፡ ' አንተ የመጽሐፍ ባለቤት ወደሆኑ ህዝቦች ትሄዳለህ። ስለዚህም እነርሱ ዘንድ ስትደርስ ከአሏህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን ወደ መመስከር ጥሪ አድርግላቸው። እነሱ ለዚህ ጥሪህ ታዛዥ ከሆኑ አሏህ በነሱ ላይ በቀንና ምሽቱ ሁሉ አምስት ሶላቶችን ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው። ለዚህ ጥሪህም ታዛዥ ከሆኑ አላህ በነሱ ላይ ከሀብታሞቻቸው ተይዞ ወደ ድሆቻቸው የምትሰጥ ምፅዋት ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው። ለዚህ ጥሪህም ታዛዦች ከሆኑ አደራህን ውድ የሆኑ ንብረቶቻቸውን (ገንዘቦቻቸውን) ተጠንቀቅ! የተበዳይንም ልመና ተጠንቀቅ! እነሆ በሷና በአላህ መሀል ግርዶሽ የለምና።'"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1496]
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙዐዝ ቢን ጀበልን - ረዲየሏሁ ዐንሁ - ወደ አላህ መንገድ ተጣሪና አስተማሪ በማድረግ ወደ የመን በላኩበት ወቅት ከክርስቲያን የሆኑ ህዝቦችን ስለሚጋፈጥ እነርሱን በተመለከተ ዝግጁ እንዲሆን አሳሰቡት። ቀጥለውም ዳዕዋውን እጅግ አንገብጋቢ ከሆነው ነጥብ እንዲጀምር ነገሩት። መጀመርያ "ላ ኢላሃ ኢለሏህ ሙሐመዱን ረሱሉሏህ" ብለው በአሏህ አንድነትና በሙሐመድ መልዕክተኝነት በመመስከር እምነታቸውን እንዲያስተካክሉ ጥሪ እንዲያደርግ፤ ምክንያቱም ወደ እስልምና የሚገቡት በዚህ የምስክርነት ቃል ስለሆነ ነው። ይህንንም ተግባራዊ ካደረጉ ሶላትን እንዲሰግዱ ማዘዝ እንዳለበት ነገሩት። ምክንያቱም ከተውሒድ በኋላ ትልቁ ግዴታ ይህ በመሆኑ ነው። ሶላትንም ካስተካከሉ በኋላ ከመካከላቸው ያሉት ባለ ፀጎች በመካከላቸው ላሉት ድሆች ከገንዘባቸው ዘካን እንዲያወጡ ማዘዝ እንዳለበት ነገሩት። ከዚያም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለዘካ ብሎ ከውድ ንብረታቸው እንዳይወስድ አስጠነቀቁት። ምክንያቱም የመስጠት ግዴታቸው ከመካከለኛ ንብረታቸው ነውና። ከዚያም የተበዳይ ዱዓእ ተቀባይነቱ ከፍተኛ በመሆኑ ተበዳይ ዱዓእ እንዳያደርግበት ግፍን መጠንቀቅ እንዳለበት አሳሰቡት።