عَنْ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما قَالَ:
قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ غَدَاةَ الْعَقَبَةِ وَهُوَ عَلَى نَاقَتِهِ: «الْقُطْ لِي حَصًى» فَلَقَطْتُ لَهُ سَبْعَ حَصَيَاتٍ، هُنَّ حَصَى الْخَذْفِ، فَجَعَلَ يَنْفُضُهُنَّ فِي كَفِّهِ وَيَقُولُ: «أَمْثَالَ هَؤُلَاءِ فَارْمُوا» ثُمَّ قَالَ: «أَيُّهَا النَّاسُ، إِيَّاكُمْ وَالْغُلُوَّ فِي الدِّينِ، فَإِنَّما أَهْلَكَ مَنْ كَانَ قَبْلَكُمْ الْغُلُوُّ فِي الدِّينِ».
[صحيح] - [رواه ابن ماجه والنسائي وأحمد] - [سنن ابن ماجه: 3029]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የጀምረተል ዐቀባህ መወርወሪያ ንጋት ላይ ግመላቸው ላይ ሆነው 'ጠጠር ልቀምልኝ!' አሉኝ። ሰባት ጠጠርም ለቀምኩላቸው። እነርሱም ትናንሽ በጣት መሀል የሚወረወሩ ጠጠሮች ነበሩ። መዳፋቸው ላይ አኑረው እያገላበጧቸውም 'እንደነዚህ ልክ ወርውሩ!' አሉ። ቀጥለውም 'እናንተ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ ተጠንቀቁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው በሃይማኖት ላይ ወሰን ማለፍ ነው።' አሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ኢብኑ ማጀህ፣ ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ኢብኑ ማጀህ - 3029]
ኢብኑ ዓባስ (ረdiየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - የመሰናበቻ ሐጅ ወቅት የእርድ ቀን ጀምረተል ዐቀባ ንጋት ላይ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር እንደነበረ ተናገሩ። የሚወረውሩት ጠጠር እንዲለቅምላቸው አዘዙት። እርሱም ሰባት ጠጠሮች ለቀመላቸው። እያንዳንዱም ጠጠር የሽንብራ ወይም የለውዝ ፍሬ መጠን ነበር ያላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በእጃቸው ላይ አኑረውት ጠጠሮቹን መደፋቸው ላይ እያንከባለሉ እንዲህ አሉ: የምትወረውሩት ጠጠር በዚህ ልክ ይሁን። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ወሰን ከማለፍና ከማክረር አስጠነቀቁ። የቀደሙ ህዝቦችን ያጠፋው ወሰን ማለፍና በሃይማኖት ላይ ከልክ በላይ ማክረር መሆኑንም ተናገሩ።