عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَا تَبْدَؤوا الْيَهُودَ وَلَا النَّصَارَى بِالسَّلَامِ، فَإِذَا لَقِيتُمْ أَحَدَهُمْ فِي طَرِيقٍ فَاضْطَرُّوهُ إِلَى أَضْيَقِهِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2167]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን በሰላምታ አትጀምሯቸው። ከመካከላቸው አንዱን መንገድ ላይ ባገኛችሁ ጊዜም ወደ ጠባቡ መንገድ አጣብቡት።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2167]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአይሁዶችና ከክርስቲያኖች ውጪ ያለ ከሃዲ ይቅርና እነርሱን ራሱ በቃልኪዳን የሚኖሩ እንኳን ቢሆኑ ለነርሱ ቀድሞ ሰላምታ ማቅረብን ከለከሉ። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከነርሱ መካከል አንዱን መንገድ ላይ ስናገኘው ወደ ጠባቡ መንገድ እንድናስጠጋው ገለፁ። መሃል መንገዱን ይዞ መሄድ ያለበት አማኝ ነው። ከመሃል መንገድ ዘወር የሚለው ከሃዲው ነው። በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን ሙስሊም የተናነሰ መሆን የለበትም።