عنْ ابنِ مَسْعُودٍ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ:
كُنَّا مَعَ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي سَفَرٍ، فَانْطَلَقَ لِحَاجَتِهِ، فَرَأَيْنَا حُمَّرَةً مَعَهَا فَرْخَانِ، فَأَخَذْنَا فَرْخَيْهَا، فَجَاءَتِ الْحُمَرَةُ فَجَعَلَتْ تَفْرِشُ، فَجَاءَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ: «مَنْ فَجَعَ هَذِهِ بِوَلَدِهَا؟ رُدُّوا وَلَدَهَا إِلَيْهَا»، وَرَأَى قَرْيَةَ نَمْلٍ قَدْ حَرَّقْنَاهَا، فَقَالَ: «مَنْ حَرَّقَ هَذِهِ؟» قُلْنَا: نَحْنُ. قَالَ: «إِنَّهُ لَا يَنْبَغِي أَنْ يُعَذِّبَ بِالنَّارِ إِلَّا رَبُّ النَّارِ».
[صحيح] - [رواه أبو داود] - [سنن أبي داود: 2675]
المزيــد ...
ከኢብኑ መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡-
«ጉዞ ላይ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ነበርን። እርሳቸው ለመፀዳዳት ሄዱ። እኛም ትንሽዬን ወፍ ከነሁለት ጫጩቶቿ ተመለከትንና ጫጩቶቿን ወሰድን። ወፏም ክንፏን እያራገበች በራ መጣች። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "ይህቺን ወፍ ልጆቿን ወስዶ ያስደነገጣት ማነው? ልጆቿን መልሱላት።" ጉንዳኖች ወረውት በእሳት ያቃጠልነውን ስፍራም ተመልክተው እንዲህ አሉ: "ይህንንስ ያቃጠለው ማነው?" እኛም "እኛ ነን።" አልን። እርሳቸውም: " እነሆ የእሳት ጌታ ካልሆነ በቀር ማንም በእሳት መቅጣት አይገባውም።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 2675]
ዐብደላህ ቢን መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት ጉዞ ላይ ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ሳሉ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለመፀዳዳት ሄዱ። ሶሓቦችም ትንሽዬ ወፍ ከነሁለት ጫጩቶቿ አገኙና ጫጩቶቹን ይዘው ሄዱ። ወፏም ጫጩቶቿን በማጣት ድንጋጤ ክንፏን እያራገበችና ዘርግታ እየበረረች መጣች። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - መጡና እንዲህ አሉ: ማነው ልጆቿን በመውሰድ ያሳዘናትና ያስፈራራት? ቀጥሎ እንዲመለሱላት አዘዙ። ቀጥለው በእሳት የተቃጠለ ጉንዳኖች የወረሩት ስፍራ ተመለከቱ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ማነው ይህንን ያቃጠለው?" አሉ። አንዳንድ ሶሓቦችም "እኛ ነን።" አሉ። እርሳቸውም "እሳትን ከፈጠረው ከአላህ በቀር አንድም ሰው በህይወት ያለን በእሳት ሊቀጣ አይፈቀድለትም።" አሉ።