+ -

عَنْ جَرِيرِ بْنِ عَبْدِ اللهِ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
سَأَلْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنْ نَظَرِ الْفُجَاءَةِ فَأَمَرَنِي أَنْ أَصْرِفَ بَصَرِي.

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2159]
المزيــد ...

ከጀሪር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
«የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለድንገተኛ እይታ ጠየቅኳቸው። እርሳቸውም አይኔን እንዳዞር አዘዙኝ።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2159]

ትንታኔ

ጀሪር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ልጅ ባዳ ሴትን ሳያስበው በድንገት በማየቱ ጉዳይ ጠየቀ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዳወቀ ፊቱን ወደሌላ አቅጣጫ ማዞር ግዴታው መሆኑን አሳሰቡት። ይህን ካደረገም ወንጀል እንደማይኖርበት ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አይንን በመስበር መታዘዙን እንረዳለን።
  2. ዓይኑ ማየቱ ክልክል ወደ ሆነ ነገር ሳያስበው በድንገት ካረፈ አትኩሮ ከመመልከት መከልከሉን እንረዳለን።
  3. እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ሶሐቦች ዘንድ ሴቶችን የመመልከት ክልክልነት የተረጋገጠ ጉዳይ እንደነበር ያስረዳናል። የዚህም ማስረጃው ጀሪር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጠየቀው ሳያስበው ዓይኑ ሴት ልጅ ላይ ቢያርፍ ብይኑ አስቦ እንዳየው ነውን? የሚል ነበርና ነው።
  4. ይህ ሐዲሥ ሸሪዓ ሰዎችን ለሚጠቅም ነገር እንዴት ትኩረት እንደሰጠ ያስረዳናል። ሴትን ልጅ ማየት ዱንያዊና አኺራዊ ጉዳት ስለሚያስከትል ሸሪዓ ሴትን ከመመልከት ከለከለ።
  5. ሶሐቦች አስቸጋሪ ጥያቄ ሲያጋጥማቸው ወደ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ተመልሰው እንደሚጠይቁ እንረዳለን። ልክ እንደዚሁ ዛሬም ሙስሊሞች አስቸጋሪ ጉዳይ ሲያጋጥማቸው ወደ ዑለማዎች ተመልሰው መጠየቅ ይገባቸዋል።