عَنْ هِشَامِ بْنِ حَكِيمِ بْنِ حِزَامٍ رَضيَ اللهُ عنهما أَنَّهُ مَرَّ عَلَى أُنَاسٍ مِنَ الْأَنْبَاطِ بِالشَّامِ، قَدْ أُقِيمُوا فِي الشَّمْسِ، فَقَالَ: مَا شَأْنُهُمْ؟ قَالُوا: حُبِسُوا فِي الْجِزْيَةِ، فَقَالَ هِشَامٌ: أَشْهَدُ لَسَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إِنَّ اللهَ يُعَذِّبُ الَّذِينَ يُعَذِّبُونَ النَّاسَ فِي الدُّنْيَا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2613]
المزيــد ...
ከሂሻም ቢን ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው: ሂሻም በሻም ውስጥ በሚገኙ ዐረብ ባልሆኑ ገበሬዎች ፀሐይ ላይ እንዲቆሙ በተደረጉ ሰዎች በኩል አለፈ። እርሱም: "ምን ሆነው ነው?" አለ። ሰዎችም "ግብር ባለመክፈላቸው ለቅጣት እዚሁ ታስረው ነው።" ብለው መለሱለት። ሂሻምም «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ እንደሰማው እመሰክራለሁ:
"እነዚያን በዱንያ ውስጥ ሰዎችን የሚቀጡን ሰዎች አላህ ይቀጣቸዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2613]
ሂሻም ቢን ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- ዐረብ ባልሆኑ ገበሬዎች በኩል ሲያልፍ ከፀሐይ ሐሩር በታች እንዲቆሙ ተደርገው ተመለከተ። ስለ ሁኔታቸውም ጠየቀ። ይህ የተደረገባቸው ግብር መክፈል እየቻሉ ባለመክፈላቸው እንደሆነም ተነገረው። ሂሻምም -አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና- ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ እንደሰማው እመሰክራለሁ አለ: አላህ ያለ አግባብ በግፍ በዱንያ ውስጥ ሌሎችን የሚቀጡ ሰዎችን ይቀጣቸዋል።