+ -

عَنْ جَابِرٍ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إِنَّ الشَّيْطَانَ قَدْ أَيِسَ أَنْ يَعْبُدَهُ الْمُصَلُّونَ فِي جَزِيرَةِ الْعَرَبِ، وَلَكِنْ فِي التَّحْرِيشِ بَيْنَهُمْ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2812]
المزيــد ...

ከጃቢር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦
"ሸይጧን በጀዚረተል ዐረብ (በባህር የተከበበው የዐረብ ምድር) ውስጥ ሰጋጆች ያመልኩኛል የሚለውን ተስፋ ቆርጧል። ነገር ግን በሰጋጆች መካከል ማጣላትን (ተስፋ አልቆረጠም)።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2812]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በጀዚረተል ዐረብ ኢብሊስ ሰጋጅ አማኞች እርሱን ወደ ማምለክና ለጣዖት ወደ መስገድ ይመለሳሉ የሚለውን ተስፋ እንደቆረጠ፤ ነገር ግን በጭቅጭቅ፣ በፀብ፣ በጦርነት፣ በፈተናና በመሳሰሉት በመካከላቸው ለማጣላት ተስፋ ከማድረግ፣ ከመታገል፣ ከመልፋት፣ ከመስራትና ከመጣር አለተወገደም ብለው ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሸይጧን አምልኮ የሚባለው የጣዖት አምልኮ ነው። ምክንያቱም በርሱ የሚያዘውም ወደርሱ ጥሪ የሚያደርገውም ሸይጧን ነውና። ይህም አላህ ስለ ኢብራሂም (ዐለይሂ ሰላም) ንግግር እንዲህ ያለውን ማስረጃ በማድረግ ነው። {አባቴ ሆይ! ሸይጧንን አትገዛ ...}
  2. ሸይጧን በሙስሊሞች መካከል ጭቅጭቅ፣ ፀብ፣ ጦርነትና ፈተናዎች እንዲከሰቱ እንደሚለፋ እንረዳለን።
  3. በእስልምና ውስጥ በሶላት ከሚገኙ ጥቅሞች መካከል በሙስሊሞች መካከል ውዴታን ትጠብቃለች፤ በመካከላቸው ያለውን የወንድማማችነት ገመድም ታጠነክራለች።
  4. ሶላት ከሁለቱ የምስክር ቃላት በኋላ ትልቁ የእስልምና ምልክት ነው። ስለዚህም ሐዲሡ ውስጥ ሙስሊሞችን ሰጋጆች በሚል ነው የጠቀሳቸው።
  5. ጀዚረተል ዐረብ ከሌሎች ሀገሮች የተለየ መለዮ እንዳላት እንረዳለን።
  6. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና (ሸይጧን በጀዚረተል ዐረብ ውስጥ ሰጋጆች ያመልኩኛል ከሚለው ተስፋ ቆርጧል። ....) ከማለታቸውም ጋር በአንዳንድ የጀዚረተል ዐረብ ክፍሎች ውስጥ የጣዖት አምልኮ ተከስቶ የለም ወይ? ከተባለ። ይህ ንግግራቸው የሚመለከተው በርካታ ሀገራቶች በሙስሊሞች በተከፈቱበትና ሰዎች ወደ አላህ ሃይማኖት በህብረት በገቡበት ወቅት የተከሰተውን የሸይጧን ተስፋ መቁረጥን ነው። ሐዲሡ የተናገረው በሸይጧን በኩል ያለውን ጥርጣሬ ነው። ከዚያም ግን አላህ ለፈለገው ጥበብ ከዚህ ተቃራኒ ተከሰተ።