عَنْ أَبِي ذَرٍّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّهُ سَمِعَ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«لاَ يَرْمِي رَجُلٌ رَجُلًا بِالفُسُوقِ، وَلاَ يَرْمِيهِ بِالكُفْرِ، إِلَّا ارْتَدَّتْ عَلَيْهِ، إِنْ لَمْ يَكُنْ صَاحِبُهُ كَذَلِكَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6045]
المزيــد ...
ከአቡዘር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እርሱ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምተዋል:
"አንድ ሰው ሌላን ሰው በአመፀኝነትም ሆነ በከሃዲነት አያነውረውም ባለቤቱ እንደዚያ ካልሆነ ወደርሱ ብትመለስ እንጂ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6045]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሌላ ሰው "አንተ አመፀኛ" ወይም "አንተ ከሃዲ" ያለ ሰው ያ ሰው እንደተናገረው ካልሆነና ለተጠቀሰው ባህሪ የተገባ ካልሆነ ንግግሩ ወደራሱ የሚመለስ መሆኑን አስጠነቀቁ። እንደተናገረው ከሆነ ግን በተናገረው ንግግር እውነተኛ ስለሆነ አንድም ነገር ወደርሱ አይመለስበትም።