عن عائشة رضي الله عنها قالت:
كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَذْكُرُ اللهَ عَلَى كُلِّ أَحْيَانِهِ.

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 373]
المزيــد ...

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች:
"ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ሁኔታቸው አላህን ያወሱ ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 373]

ትንታኔ

የአማኞች እናት ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህን በማውሳት ላይ እጅግ የሚጥሩ እንደነበሩና በሁሉም ወቅት፣ ስፍራና ሁኔታ ላይ ሆነውም አላህን ያወሱ እንደነበር ተናገረች።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህን ለማውሳት ከትንሹም ሆነ ከትልቁ ሐደሥ መፅዳት መስፈርት አይደለም።
  2. ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህን በማውሳት ላይ ዘውታሪ እንደነበሩ እንረዳለን።
  3. መፀዳዳትን በመሰለ አላህን ማውሳት በሚከለከልባቸው ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከመከተል አኳያ በሁሉም ሁኔታ ላይ አላህን ማውሳት በማብዛት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (62)
ተጨማሪ