+ -

عَنْ أَنَسٍ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِذَا تَوَضَّأَ أَحَدُكُمْ وَلَبِسَ خُفَّيْهِ فَلْيُصَلِّ فِيهِمَا، وَلْيَمْسَحْ عَلَيْهِمَا ثُمَّ لَا يَخْلَعْهُمَا إِنْ شَاءَ إِلَّا مِنْ جَنَابَةٍ».

[صحيح] - [رواه الدارقطني] - [سنن الدارقطني: 781]
المزيــد ...

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"አንዳችሁ ዉዱእ አድርጎ ኹፎቹን የለበሰ እንደሆነ እነርሱን እንደለበሰ ይስገድ። በነርሱም ላይ ያብስና ከዚያም ለጀናባ ካልሆነ በቀር ከፈለገ አያውልቃቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።] - [ሱነን ዳረቁጥኒይ - 781]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም ውዱእ አድርጎ ኹፎቹን ከለበሰ በኋላ ዉዱኡን አፍርሶ ዉዱእ ማድረግ ከፈለገ ኹፎቹ ላይ ማበስ እንደሚችል፣ ለተገደቡ ጊዜያትም ሳያወልቃቸው እነርሱን እንደለበሰ መስገድ እንደሚችል ገለፁ። ጀናባ ካጋጠመው ግን ኹፉን አውልቆ የመታጠብ ግዴታ አለበት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ኹፎቹ የተሟላ ዉዱእ ካደረጉ በኋላ የተለበሱ ካልሆኑ በቀር በነርሱ ላይ ማበስ አይፈቀድም።
  2. የማበሻ ጊዜ ገደብ ሀገሩ ለተቀመጠ ሰው አንድ ቀን ከነሌሊቱ ሲሆን ጉዞ ላይ ላለ ሰው ደግሞ ሶስት ቀን ከነሌሊቱ ነው።
  3. በኹፎች ላይ ማበስ የሚፈቀደው ዉዱእ የሚያስደርግ ነገር ሲያጋጥመን እንጂ ገላ የሚያስታጥብ ነገር ሲያጋጥም አይደለም። ገላ የሚያስታጥብ ነገር ሲያጋጥም ማበስ አይፈቀድም። ይልቁንም የግድ ሁለቱን ኹፎች ማውለቅና እግሮቹንም ማጠብ ይኖርበታል።
  4. ኹፎችን፣ ጫማዎችንና የመሳሰሉትን ለብሶ መስገድ የሁዶችን ለመቃረን ሲባል ይወደዳል። ይህ ግን ንፁህ የሆነ ጊዜ፣ ሰጋጆችንና መስጂድን የሚያውክ ነገር የሌለው ጊዜ ነው። ለምሳሌ መስጂዱ ምንጣፍ የተነጠፈበት ጊዜ ጫማውን ለብሶ አይሰግድም።
  5. በሁለቱ ኹፎች ላይ ማበስ መፈቀዱ በውስጡ ለዚህ ኡመት ማግራራትና ማቅለልን ይዟል።