+ -

عَنْ عُقْبَةَ بْنِ عَامِرٍ رضي الله عنه قَالَ: كَانَتْ عَلَيْنَا رِعَايَةُ الْإِبِلِ فَجَاءَتْ نَوْبَتِي فَرَوَّحْتُهَا بِعَشِيٍّ فَأَدْرَكْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَائِمًا يُحَدِّثُ النَّاسَ فَأَدْرَكْتُ مِنْ قَوْلِهِ:
«مَا مِنْ مُسْلِمٍ يَتَوَضَّأُ فَيُحْسِنُ وُضُوءَهُ، ثُمَّ يَقُومُ فَيُصَلِّي رَكْعَتَيْنِ، مُقْبِلٌ عَلَيْهِمَا بِقَلْبِهِ وَوَجْهِهِ، إِلَّا وَجَبَتْ لَهُ الْجَنَّةُ» قَالَ فَقُلْتُ: مَا أَجْوَدَ هَذِهِ، فَإِذَا قَائِلٌ بَيْنَ يَدَيَّ يَقُولُ: الَّتِي قَبْلَهَا أَجْوَدُ، فَنَظَرْتُ فَإِذَا عُمَرُ قَالَ: إِنِّي قَدْ رَأَيْتُكَ جِئْتَ آنِفًا، قَالَ: «مَا مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ يَتَوَضَّأُ فَيُبْلِغُ - أَوْ فَيُسْبِغُ - الْوَضُوءَ ثُمَّ يَقُولُ: أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَأَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُ اللهِ وَرَسُولُهُ إِلَّا فُتِحَتْ لَهُ أَبْوَابُ الْجَنَّةِ الثَّمَانِيَةُ يَدْخُلُ مِنْ أَيِّهَا شَاءَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 234]
المزيــد ...

ከዑቅባ ቢን ዓሚር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «በመካከላችን የምንሰራው የግመል እረኝነት ነበር። የኔ ተራ ደረሰና ግመሎቹን በቀኑ መጨረሻ ወደ ማደሪያቸው አስገባሁና የአላህ መልክተኛን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቆመው ለሰዎች እየተናገሩ ደረስኩ። ይህንን ሲናገሩም ደረስኩባቸው:
"ዉዱኡን አሳምሮ የሚያደርግና ከዚያም በቀልቡም በፊቱም ወደ አላህ ተመልሶ ቆሞ ሁለት ረከዓ የሚሰግድ አንድም ሙስሊም የለም ለርሱ ጀነት ግዴታ (ተገቢ የሆነች) ብትሆንለት እንጂ።" እኔም "ይህቺ ንግግር ምን ያማረች ናት!" አልኩኝ። ይህን ጊዜም ከፊቴ ያለ ሰው "ከዚሁ በፊት የተናገሯት ደግሞ እጅግ ያማረች ናት።" አለ። ስመለከተው ዑመር ነው። እንዲህም አለኝ "እኔ ገና አሁን እንደመጣህ አይቻለሁ ከመምጣትህ በፊት ያሉት እንዲህ ነው: 'ከናንተ መካከል አንድም ዉዱእን አዳርሶ የሚያደርግና ከዚያም ‹አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱላሂ ወረሱሉህ› የሚል የለም ለርሱ ስምንቱ የጀነት በሮች የሚከፈቱና በፈለገው በር የሚገባ ቢሆን እንጂ።'"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 234]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለሰዎች ሲናገሩ ሁለት ትላልቅ ደረጃዎችን ገለፁ።
የመጀመሪያው: ዉዱእን በተደነገገው መልኩ አሳምሮ፣ አዳርሶ፣ አሟልቶ ያደረገ፤ ለሁሉም አካል የሚገባውን ውሃ የሰጠ ቀጥሎም «አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱላሂ ወረሱሉህ» ያለ ሰው በፈለገው በር እንዲገባ ለርሱ ስምንቱም የጀነት በሮች የሚከፈቱለት መሆናቸውን ነው።
ሁለተኛ: ይህንን የተሟላ ውዱእ ያደረገና ቀጥሎ ከዚህ ዉዱእ በኋላ በቀልቡ ወደ አላህ ዞሮ፣ ለአላህ አጥርቶና ተመስጦ፣ በፊቱም በመላ አካሉም ተዋድቆ ሁለት ረከዓ ቆሞ ለአላህ የሚሰግድ ለርሱ ጀነት ግድ እንደምትሆንለት ይፋ አደረጉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህ በትንሽ ስራ ትልቅ ምንዳን መስጠቱ የርሱን ትልቅ ችሮታ ያስረዳናል።
  2. ዉዱእን ማዳረስና መሙላት፣ ቀጥሎም በተመስጦ ሁለት ረከዓ መስገድ መደንገጉንና በርሱም የሚገኘው ምንዳ ታላቅ መሆኑን እንረዳለን።
  3. ዉዱእን ማዳረስና ቀጥሎ ይህንን ዚክር ማለት ወደ ጀነት መግቢያ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው።
  4. ገላውን ለሚታጠብ ሰውም ይህንን ዚክር ማለቱ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  5. ሶሐቦች እውቀት በመፈለግ ላይ፣ በማሰራጨቱ ላይ፣ እንዲሁም በኑሯዊ ጉዳዮችና በመሰል መልካም ነገሮች ላይ ሁሉ የነበራቸውን ትብብር እንረዳለን።
  6. ዉዱእ በማድረግ ውስጥ አካልን ማፅዳትና፣ ሰውነትን ከቆሻሻ ማጥራት እንደሚገኘው ሁሉ ከዉዱእ በኋላ ያለውን ዚክር በማለት ደሞ ቀልብን ከሽርክ ማፅዳትና ማጥራት ይገኝበታል።