عَنْ أَنَسٍ رضي الله عنه قَالَ:
كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَغْسِلُ، أَوْ كَانَ يَغْتَسِلُ، بِالصَّاعِ إِلَى خَمْسَةِ أَمْدَادٍ، وَيَتَوَضَّأُ بِالْمُدِّ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 201]
المزيــد ...
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
"ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገላቸውን ከአንድ ቁና ውሃ እስከ አምስት እፍኝ ድረስ ባለ ውሃ ያጥቡ ወይም ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዹእ ያደርጉ ነበር።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 201]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአንድ ቁና እስከ አምስት እፍኝ በሚደርስ ውሃ ከጀናባ ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዱእ ያደርጉ ነበር። ቁና ማለት አራት እፍኝ ውሃ ማለት ሲሆን እፍኝ ማለት ደግሞ መካከለኛ ተፈጥሮ ያለው ሰው በሁለቱ መዳፎቹ ሙሉ የሚያክል ነው።