عَنْ جَابِرٍ رضي الله عنه قال: أَخْبَرَنِي عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ:
أَنَّ رَجُلًا تَوَضَّأَ فَتَرَكَ مَوْضِعَ ظُفُرٍ عَلَى قَدَمِهِ فَأَبْصَرَهُ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ: «ارْجِعْ فَأَحْسِنْ وُضُوءَكَ» فَرَجَعَ، ثُمَّ صَلَّى.
[صحيح بشواهده] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 243]
المزيــد ...
ከጃቢር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው: እንዲህ አለ: "ዑመር ቢን አልኸጧብ እንዲህ ብሎ ነገረኝ:
'አንድ ሰውዬ ውዱእ አደረገና እግሩ ላይ ጥፍር የምታክል ስፍራ ተወ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተመለከቱትና እንዲህ አሉት: ‹ተመለስና ዉዱእህን አሳምር!› ተመልሶ (አስተካከለና) ከዚያም ሰገደ።'"
[በማመሳከሪያዎቹ ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 243]
ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ዉዱእ አድርጎ የጨረሰን ሰውዬ እግሩ ላይ ጥፍር የምታክል የዉዱእ ውሃ ያልነካት ስፍራን እንደተመለከቱበት ተናገሩ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወደ ተወው ስፍራ እየጠቆሙ እንዲህ አሉት: ተመለስና ዉዱእህን አሳምር! አሟልተህ አድርግ! ለሁሉም አካልህ ከውዱኡ ውሃ የሚገባውን ሐቅ ስጠው አሉት! ሰውዬውም ተመለሰና ዉዱኡን አሟልቶ ሰገደ።