عَنْ المُغِيرَةِ رضي الله عنه قَالَ:
كُنْتُ مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي سَفَرٍ، فَأَهْوَيْتُ لِأَنْزِعَ خُفَّيْهِ، فَقَالَ: «دَعْهُمَا، فَإِنِّي أَدْخَلْتُهُمَا طَاهِرَتَيْنِ» فَمَسَحَ عَلَيْهِمَا.

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከሙጊራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል:
"አንድ ጉዞ ላይ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩና ኹፋቸውን (የቆዳ ካልሲያቸውን) ላወልቅ ዝቅ አልኩ፤ እሳቸውም: ' እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።' አሉኝና በነርሱ ላይ አበሱ።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim. This is the wording of Al-Bukhari]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአንድ ጉዟቸው ላይ ሳሉ ዉዱእ አደረጉ። ሁለት እግራቸውን ማጠብ ላይ በደረሱ ጊዜ ሙጚራ ቢን ሹዕባ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እግራቸውን እንዲያጥቡ ብለው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አድርገውት የነበረውን ኹፍ ሊያወልቁ እጃቸውን ዘረጉ ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "አታውልቃቸው ተዋቸው! እኔ ሁለት እግሬን ኹፎቹ ውስጥ ያስገባሁት በጦሀራ ላይ ሁኜ ነው " አሏቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እግራቸውን በማጠብ ምትክ ኹፋቸውን አበሱ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሁለት ኹፎች ላይ ማበስ የተደነገገው ከትንሹ ሐደሥ (ዉዱእ አጥፍቶ) ዉዱእ በሚደረግበት ወቅት ነው። ለትልቁ ሐደሥ (ገላን ለሚያስታጥብ ጉዳይ) መታጠብ አስፈላጊ በሆነበት ጊዜ ግን የግድ ሁለት እግሮችን መታጠብ ይኖርበታል።
  2. ኹፍ ላይ ማበስ የሚገኘው በውሃ በረጠበ እጅ ታችኛውን ሳይሆን ላይኛውን የኹፉ ክፍል አንድ ጊዜ በመዳበስ ነው።
  3. በሁለት ኹፎች ላይ ለማበስ ሊሟሉ የሚገቡ መስፈርቶች አሉ። እነሱም: ኹፎቹን የሚለብሰው ሁለት እግሮቹን በውሃ ካጠበበት የተሟላ ዉዱእ በኋላ መሆን ይገባዋል፤ ኹፉ ንፁህና በትጥበት ወቅት ማጠብ ግዴታ የሆነውን የእግሩን ክፍል የሸፈነ መሆን ይገባዋል፤ የሚያብሰው በጀናባ (የዘር ፈሳሽ መጥቶት ወይም ግንኙነት በማድረጉ) ወይም ገላን የሚያስታጥቡ ነገሮች ሲያጋጥሙት ሳይሆን በትንሹ ሐደሥ (ውዱእ የሚያስደርጉ ምክንያቶች ሲያጋጥሙት) ብቻ መሆን ይገባዋል፤ የሚያብሰውም በሸሪዓ በተወሰነው ወቅት መሆን ይገባዋል። እሱም መንገደኛ ላልሆነ አንድ ቀን ከነምሽቱ ሲሆን ጉዞ ላይ ላለ ደግሞ ሶስት ቀን ከነሌሊቱ ነው።
  4. እንደካልሲና የመሳሰሉት ሁለት እግሮችን የሚሸፍኑ ሁሉ እንደ ሁለቱ ኹፎች ተመሳሳይ ፍርድ ስላላቸው በነርሱ ላይም ማበስ ይበቃል።
  5. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙጚራ ኹፋቸውን እንዳያወልቅ ሲከለክሉት ነፍሱ እንድትረጋጋና ብይኑን እንዲያውቅ ምክንያታቸውን መግለፃቸው የርሳቸው ስነምግባርና የማስተማር መንገዳቸው ማማሩን ያስረዳናል።