عَنْ حُذَيْفَةَ رضي الله عنه قَالَ:
كُنْتُ مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَانْتَهَى إِلَى سُبَاطَةِ قَوْمٍ، فَبَالَ قَائِمًا، فَتَنَحَّيْتُ فَقَالَ: «ادْنُهْ» فَدَنَوْتُ حَتَّى قُمْتُ عِنْدَ عَقِبَيْهِ فَتَوَضَّأَ فَمَسَحَ عَلَى خُفَّيْهِ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 273]
المزيــد ...
ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ነበርኩ። ወደ ቆሻሻ መጣያ ዘንድ ሲደርሱ ቆመው ሸኑ። ከርሳቸው ገሸሽ ስል "ቅረብ" አሉኝ። እግራቸው አጠገብ እስከምቆም ድረስ ቀረብኩ። ዉዱእ አደረጉና በኹፋቸው ላይ አበሱ።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 273]
ሑዘይፋ ቢን አልየማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሳለ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መሽናት ፈለጉና የቆሻሻ መጣያ ስፍራ ገቡ። የአብዛኛው ጊዜ ልማዳቸው ተቀምጦ መሽናት ቢሆንም ቆመው ሸኑ።
ሑዘይፋም ከርሳቸው ራቅ አለ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ቀረብ በል!" አሉት። ሑዘይፋም በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከእይታ ሊጋርዳቸው ከኋላቸው ተረከዛቸው አጠገብ እስኪቆም ድረስ ቀረባቸው።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጥለው ዉዱእ አደረጉ። እግራቸውን የሚታጠቡበት ቦታ ላይ ሲደርሱም ኹፋቸውን ሳያወልቁ በላዩ ላይ በማበስ ብቻ ተብቃቁ። ኹፍ ማለት ከቀጭን ቆዳ ወይም ከመሳሰሉት የሚሰራ እግር ላይ የሚጠለቅና እስከ ቁርጭምጭሚት ድረስ የሚለበስ ካልሲ ነው።