+ -

عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رضي الله عنهما قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَا يَنْظُرُ اللهُ إِلَى رَجُلٍ أَتَى رَجُلًا أَوِ امْرَأَةً فِي دُبُرٍ».

[صحيح] - [رواه الترمذي والنسائي في الكبرى] - [السنن الكبرى للنسائي: 8952]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"አላህ ወንድን ልጅ ወይም ሴትን ልጅ በመቀመጫ የተገናኘን ሰው (በእዝነት) አይመለከተውም።"

[ሶሒሕ ነው።] - - [አስሱነኑል ኩብራ ነሳኢ - 8952]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን በመቀመጫቸው የተገናኘን ሰው አላህ በእዝነት እይታ እንደማያየው ከባድ ዛቻን ገለፁ። ይህ ተግባርም ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ወንድ ልጅ ከወንድ ጋር መገናኘቱ (ግብረሰዶማዊነት) መፈፀሙ ከትላልቅ ወንጀሎች አንዱ ነው።
  2. ሴትንም በመቀመጫዋ መገናኘት ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው።
  3. (አላህ አይመለከተውም) ማለት የእዝነትና የርህራሄ እይታ አያየውም ማለት ነው እንጂ አጠቃላይ የሆነ እይታ ማለት አይደለም። አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ በርሱ ላይ አንዳችም ነገር አይሰወርም። አንድም ነገር ከርሱ እይታ አይርቅም።
  4. ይህ ተግባር የሰውን ንፁህ ተፈጥሮ ስለሚፃረር፣ ዘርን ስለሚያሳንስ፣ የትዳርን ህይወት ስለሚያበላሽ፣ ጥላቻና ጠላትነትን ስለሚተክል፣ በቆሻሻ መንገድ ስለሚፈፀም በሰው ልጅ ከሚሰሩ ከትላልቅ ፀያፍና አደገኛ ተግባራት መካከል የሚመደብ ነው።