عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَلْعُون مَنْ أتَى امرأتَه في دُبُرِها».
[حسن] - [رواه أبو داود والنسائي في الكبرى وأحمد] - [سنن أبي داود: 2162]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ሚስቱን በመቀመጫዋ የተገናኛት ሰው የተረገመ ነው።"»
[ሐሰን ነው።] - [አቡዳውድ፣ ነሳኢ በኩብራ ውስጥ፣ አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 2162]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባል ሚስቱን በመቀመጫዋ በኩል መገናኘቱን ከለከሉ። ከአላህ እዝነት የተባረረና የተረገመ መሆኑንም ገለፁ። ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል የሚመደብም ነው።