عن أبي موسى رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«لا نِكَاحَ إِلّا بِوَليٍّ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 2085]
المزيــد ...
ከአቡ ሙሳ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦
"ያለ ወሊይ ፈቃድ ጋብቻ የለም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 2085]
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዲት ሴት የጋብቻዋን ውል ለማሰር ሀላፊነት በሚወስድ ወሊይ ካልሆነ በስተቀር ጋብቻ መፈፀም እንደማይበቃላት ገለፁ።