+ -

عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه قال:
عَلَّمَنَا رَسُوْلُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ خُطْبَةَ الحَاجَةِ: إِنَّ الحَمْدَ للهِ، نَسْتَعِيْنُهُ وَنَسْتَغْفِرُهُ، وَنَعُوْذُ بِهِ مِنْ شُرُوْرِ أَنْفُسِنَا، مَنْ يَهْدِ اللهُ فَلَا مُضِلَّ لَهُ، وَمَنْ يُضْلِلْ فَلَا هَادِيَ لَهُ، وَأَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا الله، وَأَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُهُ وَرَسُوْلُهُ، {يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ مِنْ نَفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي تَسَاءَلُونَ بِهِ والأرحام إن الله كان عليكم رقيبا} [النساء: 1]، {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنْتُمْ مُسْلِمُونَ} [آل عمران: 102]، {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا (70) يُصْلِحْ لَكُمْ أَعْمَالَكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ وَمَنْ يُطِعِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَقَدْ فَازَ فَوْزًا عَظِيمًا} [الأحزاب:70 - 71].

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه والنسائي وأحمد] - [سنن أبي داود: 2118]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ የጉዳይ ጊዜ ኹጥባን (ኹጥበቱል ሓጃህ) አስተማሩን: 'ኢነልሐምደ ሊላህ ነስተዒኑሁ ወነስተጝፊሩሁ ወነዑዙ ቢላሂ ሚን ሹሩሪ አንፉሲና ፤ መን የህዲላሁ ፈላሙዺለ ለሁ ወመንዩዽሊል ፈላ ሃዲየ ለሁ ፤ ወአሽሀዱ አን ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአሽሀዱ አነ ሙሓመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ሱረቱ ኒሳእ: 1፣ ኣሊ‐ዒምራን: 102፣ አል‐አሕዛብ: 70‐71'" (ትርጉሙም: ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው። እገዛን ከርሱ እንፈልጋለን። ምህረትንም ከርሱ እንፈልጋለን። ከነፍሳችን ክፋትም በርሱ እንጠበቃለን። አላህ የመራው ሰው አጥማሚ የለውም። ያጠመመውንም መሪ የለውም። ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ። ሙሐመድም የአላህ ባሪያውና መልክተኛው መሆናቸውን እመሰክራለሁ። {እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን (ሐዋን) የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ። ያንንም በርሱ የምትጠያየቁበትን አላህንና ዝምድናዎችንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ። አላህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና።} [አንኒሳእ: 1] {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት። እናንተም ሙስሊሞች ሆናችሁ እንጂ አትሙቱ።} [አሉ ዒምራን: 102] {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ። ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ። [70] ሥራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና ሀጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል። አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ። [71]} [አልአሕዛብ 70 -71])

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብኑማጀህ፣ ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 2118]

ትንታኔ

ኢብኑ መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የጉዳይ ጊዜ ኹጥባን እንዳስተማሯቸው ተናገሩ። ይህም እንደጋብቻና የጁመዓ ኹጥባ በመሰሉ ኹጥባዎችና በጉዳዮቻቸው ወቅት ንግግርን ሲጀምሩ የሚባል ነው። ይህቺ ኹጥባ አጠቃላይ የምስጋና አይነቶች አላህ እንደሚገባው፣ አጋር ከሌለው ከርሱ ብቻ እገዛን መፈለግን፣ ወንጀሎችን መሸሸግና ይቅር ማለትን ከርሱ መፈለግን፣ ከነፍስ ክፋትና ከሌሎችም ሁሉ ክፋቶች ወደርሱ መጠጋትንና ሌሎችንም ትላልቅ ሀሳቦችን ሰብስባለች።
ቀጥለውም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መመራት በአላህ እጅ መሆኑን ፤ አላህ የመራውን ሰው አጥማሚ እንደሌለው ያጠመመውንም መሪ እንደሌለው ተናገሩ።
ቀጥለውም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም የሚለውን የተውሒድን የምስክር ቃልና ሙሐመድ የአላህ ባሪያና መልክተኛ ናቸው የሚለውን የመልክተኝነትን ምስክር ቃል ጠቀሱ።
ይህንንም ኹጥባ የአላህን ፊት ፈልጎ የአላህን ትእዛዛት በመፈፀምና ክልከላውን በመራቅ አላህን በመፍራት የሚያዝ እንዲሁም ይህንን የፈፀመ ሰውም ምንዳው ስራውና ንግግሩ ይስተካከላል፣ ወንጀሎቹ ይማራሉ፣ ሀጢአቶቹ ይረግፋሉ፣ በዱንያም ያማረ ህይወት ይጎናፀፋል፣ የትንሳኤ ቀንም በጀነት ስኬትን ይቀዳጀል። የሚልን ሀሳብ በጠቀለሉ እነዚህ ሶስት አንቀፆች ቋጩት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የጋብቻን የጁመዓንና ሌሎችንም ኹጥባዎች በዚህ ኹጥባ መክፈት እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. አንድ ኹጥባ ምስጋናን ፣ ሁለቱን የምስክር ቃላቶችንና ጥቂት የቁርአን አንቀጾችን ያካተተ መሆን ይገባዋል።
  3. ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለባልደረቦቻቸው ለእምነታቸው የሚያስፈልጋቸውን ማስተማራቸውን እንረዳለን።