+ -

عن أُبيِّ بن كعبٍ رضي الله عنه قال:
صلَّى بنا رسولُ الله صلى الله عليه وسلم يومًا الصُّبحَ فقال: «أشاهِد فُلان؟» قالوا: لا، قال: «أشاهِدٌ فُلان؟» قالوا: لا، قال: «إنَّ هاتيَنِ الصَّلاتين أثقَلُ الصَّلَواتِ على المُنافقين، ولو تعلمون ما فيهما لأتيتُمُوهما ولو حَبْوًا على الرُّكب، وإن الصفَّ الأوّلَ على مِثلِ صَفِّ الملائكة، ولو عَلِمتُم ما فضيلتُه لابتَدَرتُموهُ، وإنّ صلاةَ الرجل مع الرجل أزكى من صلاتِه وحدَه، وصلاتَه مع الرجلَين أزكى من صلاتِه مع الرجل، وما كَثُرَ فهو أحبُّ إلى الله تعالى».

[صحيح] - [رواه أبو داود والنسائي وأحمد] - [سنن أبي داود: 554]
المزيــد ...

ከኡበይ ቢን ከዕብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
አንድ ቀን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሱብሒን አሰገዱንና "እከሌ አብሮን ሰግዷልን?" አሉ። ሶሐቦችም "አይ" አሉ። እርሳቸውም "እከሌስ ተሳትፏልን?" አሉ። ሶሐቦችም "አይ" አሉ። እርሳቸውም "እነዚህ ሁለት ሶላቶች በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባድ ሶላት ናቸው። በነዚህ ሶላቶች ያለውን ምንዳ ብታውቁ ኖሮ በጉልበታችሁ እየዳኻችሁም ቢሆን ትመጡ ነበር። የመጀመሪያው ሰልፍ በመላዕክት ሰልፍ አምሳያ ነው። በርሱ የሚገኘውን ደረጃ ብታውቁ ኖሮ ትቻኮሉለት ነበር። ሰውዬው ከሌላ ሰው ጋር የሚሰግደው ሶላት ብቻውን ከሚሰግደው ሶላት የተሻለ ነው። ከሁለት ሰዎች ጋር የሚሰግደው ሶላት ከአንድ ሰው ጋር ከሚሰግደው ሶላት የተሻለ ነው። ህብረቱ በበዛበት ልክ አላህ ዘንድም እጅግ ተወዳጅ ነው።" አሉ።»

[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን አቡዳውድ - 554]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ቀን ፈጅርን አሰገዱና ቀጥለው እከሌ ይህ ሶላታችን ላይ ተሳትፏልን? ብለው ጠየቁ። ሶሐቦችም "አይ" አሉ። ቀጥለውም ሌላን ሰው "እከሌስ ተሳትፏልን?" አሉ። ሶሐቦችም "አይ" አሉ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: የፈጅርና የዒሻ ሶላቶች በነርሱ ወቅት ድካም ስለሚበዛና በጨለማ ስለማይታዩ ይዩልኝን ማግኘት የሚያንስበት ወቅት ስለሆነ በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባድ ሶላቶች ናቸው።
እናንተ አማኞች ሆይ! በሱብሒና በዒሻ ሶላቶች የሚገኘውን ተጨማሪ ምንዳና አጅር ብታውቁ ኖሮ (ምንዳ የሚገኘው እንደ አድካሚነቱ ልክ ነውና።) በእጃችሁና በጉልበታችሁ እየተጎተታችሁና እየዳኸችሁ ትመጡ ነበር።
የመጀመሪያው ሰልፍ ከኢማሙ ጋር ያላቸው ቀረቤታ ልክ የመላእክቶች ሰልፍ ወደ አላህ እንዳላቸው ቀረቤታ ነው። አማኞች በመጀመሪያ ሰልፍ ያለውን ትሩፋት ቢያውቁ ኖሮ ወደርሱ ይሽቀዳደሙ ነበር። ሰውዬው ከአንድ ሰው ጋር የሚሰግደው ሶላት ለብቻው ከሚሰግደው ሶላት የበለጠ ምንዳና አጅር ያስገኝለታል። ከሁለት ሰዎች ጋር የሚሰግደው ሶላት ደሞ ከአንድ ሰው ጋር ከሚሰግደው ሶላት የበለጠ ምንዳና አጅር ያስገኝለታል። ሰጋጆች የበዙበት ሶላት ወደ አላህ እጅግ ተወዳጅና በላጭ የሆነ ሶላት ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የመስጂድ ኢማም የአማኞችን ሁኔታ መከታተልና ከነርሱ ስለራቀ ሰው ሁኔታ መጠየቁ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
  2. የጀመዓ ሶላትን ዘውትር መተግበርና በተለይ የዒሻና የፈጅር ሶላትን በጀመዓ መስገድ የኢማን ምልክት መሆኑን እንረዳለን።
  3. የዒሻና የፈጅር ሶላቶች ምንዳ ትልቅነትን እንረዳለን። ይህም ወደነርሱ መምጣት ነፍስን መታገልና በአምልኮ ላይ መታገስን ስለሚጠይቅ ነው። ስለዚህም በነርሱ የሚገኘው ምንዳ ከሌሎቹ የበለጠ ሆነ።
  4. የጀመዓ ሶላት በሁለት ሰውና ከዛ በላይ ባሉ ይታሰራል።
  5. የመጀመሪያ ሰልፍ ደረጃ መገለፁንና ወደርሱ በመቻኮልም መነሳሳቱን እንረዳለን።
  6. የጀመዓ መብዛት ያለውን ደረጃ እንረዳለን። ጀመዓው በበዛ ቁጥር ምንዳውም ይበዛልና።
  7. መልካም ስራዎች ሸሪዓው እንደማበላለጡ ልክና እንደሚገለፁበት ሁኔታ ይበላለጣሉ።