+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال:
أَتَى النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ رَجُلٌ أَعْمَى، فَقَالَ: يَا رَسُولَ اللهِ، إِنَّهُ لَيْسَ لِي قَائِدٌ يَقُودُنِي إِلَى الْمَسْجِدِ، فَسَأَلَ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنْ يُرَخِّصَ لَهُ فَيُصَلِّيَ فِي بَيْتِهِ، فَرَخَّصَ لَهُ، فَلَمَّا وَلَّى دَعَاهُ، فَقَالَ: «هَلْ تَسْمَعُ النِّدَاءَ بِالصَّلَاةِ؟» فَقَالَ: نَعَمْ، قَالَ: «فَأَجِبْ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 653]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ አንድ ማየት የተሳነው ሰውዬ መጣ። 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ወደ መስጂድ የሚመራኝ መሪ የለኝም።' በማለት የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በቤቱ መስገድን እንዲያገሩለት ጠየቀ። ለርሱም አግራሩለት። ለመሄድ የዞረ ጊዜ ጠሩትና 'የሶላትን ጥሪ ትሰማለህን?' አሉት። እርሱም 'አዎን' አላቸው። እሳቸውም 'እንግዲያውስ ለጥሪው መልስ ስጥ!' አሉት።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 653]

ትንታኔ

አንድ አይነ ስውር ሰውዬ ወደ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኔ ዘንድ ለአምስቱ ሶላቶች እጄን ይዞ ወደ መስጂድ የሚወስደኝና የሚያግዘኝ የለም።" አለ። ፍላጎቱ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀማዓን በመተው ለርሱ እንዲያግራሩለት ነው። ለርሱም አግራሩለት። ለመሄድ የዞረ ጊዜም ጠሩትና "የሶላትን አዛን ትሰማለህን?" አሉት። እርሱም "አዎን" አለ። እሳቸውም "የሶላቱን ተጣሪ ጥሪ መልስ" አሉት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Kannadisht الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ግዴታ ለሆነ ነገር ካለሆነ በቀር ማግራራት ስለማይኖር የጀማዓ ሶላት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  2. "ጥሪውን መልስ!" ከሚለው ቃላቸው አዛን የሚሰማ ሰው ላይ የጀማዓ ሶላት ግዴታ መሆኑን ይጠቁማል። ትእዛዝ በመሰረቱ የሚያስፈርደው ግዴታን ነውና።