عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«خَيْرُ صُفُوفِ الرِّجَالِ أَوَّلُهَا، وَشَرُّهَا آخِرُهَا، وَخَيْرُ صُفُوفِ النِّسَاءِ آخِرُهَا، وَشَرُّهَا أَوَّلُهَا».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 440]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ለወንዶች ምርጡ የሶላት ሰልፍ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጨረሻው ነው። ለሴቶች ምርጡ ሰልፍ የመጨረሻው ሰልፍ ነው። መጥፎው ደግሞ የመጀመሪያው ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 440]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶላት ላይ ለወንዶች ምርጡ፣ በርካታ ምንዳንና ደረጃን የሚያስገኘው ሰልፍ የመጀመሪያው ሰልፍ እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ወደ ኢማሙ ስለቀረቡ፣ የርሱን ቁርአን ስለሚሰሙና ከሴቶችም ስለራቁ ነው። መጥፎው፣ ጥቂት ምንዳና ደረጃ የሚያገኘው፣ ከሸሪዓ ዓላማ የሚርቀው ሰልፍ ደግሞ የመጨረሻው ሰልፍ ነው። የሴቶች ምርጥ ሰልፍ ደግሞ የመጨረሻው ሰልፍ እንደሆነ ተናገሩ። ይህም ለነሱ ሸሸግ የሚያደርጋቸው፣ ከወንዶች ጋር ከመቀላቀል፣ በነርሱ ከመታየት፣ በነርሱ ከመፈተንም የራቀ ስለሆነ ነው። መጥፎው ሰልፍ ደግሞ ከወንዶች ስለሚቀርብ፣ ለፈተና ስለምትጋለጥ የመጀመሪያው ሰልፍ ነው።