عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ غَدَا إِلَى الْمَسْجِدِ أَوْ رَاحَ أَعَدَّ اللهُ لَهُ فِي الْجَنَّةِ نُزُلًا، كُلَّمَا غَدَا أَوْ رَاحَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 669]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ማለዳ ላይ ወይም ከቀትር በኋላ ወደ መስጂድ የሄደ ሰው ማልዶ በሄደና ከቀትር በኋላ በሄደ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ መስተንግዶ ያዘጋጅለታል።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 669]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአምልኮም ይሁን ለእውቀት ወይም ከዚህ ውጪ ላሉ መልካም አላማዎች በመጀመሪያው የቀን ክፍልም ሆነ በመጨረሻው የቀን ክፍል በማንኛውም ወቅት መስጂድ የመጣ ሰው በቀኑ ክፍለ ጊዜ ውስጥ ወይም በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ ውስጥ መስጂድ በመጣ ቁጥር አላህ ለርሱ ጀነት ውስጥ ስፍራና መስተንግዶ እንዳዘጋጀለት አበሰሩ።