عن أبي هريرة رضي الله عنه عن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ فَلْيَقُلْ خَيْرًا أَوْ لِيَصْمُتْ، وَمَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ فَلْيُكْرِمْ جَارَهُ، وَمَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ فَلْيُكْرِمْ ضَيْفَهُ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር! በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር!"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአላህ እና መመለሻውም በስራው የሚመነዳበትም በሆነው መጨረሻው ቀን ያመነ ባሪያ ኢማኑ እነዚህን ጉዳዮችን በመፈፀም ላይ እንደሚያነሳሳው ገለፁ:
የመጀመሪያው: መልካም መናገር ነው። በዚህ ውስጥ ሱብሓነላህ ማለት፣ ላኢላሃኢለላህ ማለት፣ በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከል፣ በተጣሉ ሰዎች መካከል ማስማማት የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ። ይህንን ካልፈፀመ ዝምታን ያዘውትር፣ ክፋቱን ይቆጥብ፣ ምላሱን ይጠብቅ።
ሁለተኛ: ጉረቤትን ማክበር፡ ይህም እነሱን ባለማወክና ለነርሱ በጎ በማድረግ ነው።
ሶስተኛ: ለመዘየር የመጣን እንግዳ መልካም በማናገር፣ ምግብ በማብላትና ይህን በመሳሰሉት ማክበር ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በአላህና በመጨረሻው ቀን ማመን ለሁሉም መልካም ነገር መሰረት ነው። መልካም ተግባራትን በመፈፀም ላይም ያነሳሳል።
  2. ከምላስ ወለምታ መከልከሉን ፤
  3. የኢስላም ሃይማኖት የአንድነትና የቸርነት ሃይማኖት መሆኑን ፤
  4. እነዚህ ጉዳዮች ከኢማን ክፍሎችና ምስጉን ከሆኑ ስነስርአቶች መሆናቸውን ፤
  5. ንግግር ማብዛት ወደሚጠላ ወይም ወደተከለከለ ነገር ይጎትታል። ሰላም የሚገኘው ከመልካም ውጪ ባለመናገር እንደሆነ እንረዳለን።