عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ كَانَتْ لَهُ مَظْلَمَةٌ لِأَخِيهِ مِنْ عِرْضِهِ أَوْ شَيْءٍ فَلْيَتَحَلَّلْهُ مِنْهُ اليَوْمَ، قَبْلَ أَلا يَكُونَ دِينَارٌ وَلاَ دِرْهَمٌ، إِنْ كَانَ لَهُ عَمَلٌ صَالِحٌ أُخِذَ مِنْهُ بِقَدْرِ مَظْلَمَتِهِ، وَإِلَمْ تَكُنْ لَهُ حَسَنَاتٌ أُخِذَ مِنْ سَيِّئَاتِ صَاحِبِهِ فَحُمِلَ عَلَيْهِ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 2449]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል:
"የወንድሙን ክብር በመንካት ወይም በአንዳች ነገር ወንድሙን የበደለ ሰው ዲናርና ዲርሃም የሌለበት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬ ከራሱ ላይ በደሉን ያስነሳ። (የትንሳኤ ቀን) መልካም ስራ ካለው በበደሉ ልክ ይቀነስበታል። ለርሱ መልካም ስራ ከሌለው ከበደለው ባልደረባው ወንጀሎች ተወስደው እርሱ ላይ ይደረጋሉ።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2449]
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሙስሊም ወንድሙን በክብሩ ወይም በገንዘቡ ወይም በደሙ የበደለ ሰው ነፍሱን ለማዳን ለበደለው ሰው የሚሰጠው የወርቅ ዲናርም ሆነ የብር ዲርሃም የማይጠቅምበት የትንሳኤ ቀን ከመምጣቱ በፊት በዱንያ ውስጥ እስካለ ድረስ የተበዳዩን ይቅርታ እንዲጠይቅ አዘዙ። የትንሳኤ ቀን ፍርድ የሚሰጠው በመልካም ስራዎችና ሀጢአቶች ነውና። ተበዳዩ ከበዳዩ መልካም ስራዎች ቀንሶ የተበደለውን ያህል መልካም ስራዎችን ይወስዳል። በዳዩ መልካም ስራዎች ከሌሉት በበደሉ ልክ ከተበዳዩ ወንጀሎች ተወስደው በበዳዩ ላይ ይደረጋሉ።