عن جرير بن عبد الله رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«مَنْ لَا يَرْحَمِ النَّاسَ لَا يَرْحَمْهُ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 2319]
المزيــد ...

ከጀሪር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:
"ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2319]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለሰዎች የማይራራ ሰውን የላቀውና የተከበረው አላህም እንደማይራራለት ገለፁ። ሰው ለፍጡር ማዘኑ የአላህን ርህራሄ ማግኛ ከሆኑ ትላልቅ ሰበቦች መካከል ነው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ርህራሄ ለሌሎቹም ፍጡራን ያስፈልጋል። ነገር ግን ሀዲሡ ላይ ሰውን ብቻ የጠቀሰው አፅንኦት ለመስጠት ነው።
  2. አላህ ለአዛኝ ባሮቹ የሚራራ አዛኝ ጌታ ነው። ምንዳ በስራ አይነት ነው።
  3. ለሰው ማዘን ሲባል ለነሱ መልካም ማድረግን፣ ጉዳትን ከነርሱ ላይ መከላከልንና ባማረ መልኩ ከነርሱ ጋር መኗኗርን ይጠቀልላል።
ትርጉሞችን ይመልከቱ
ቋንቋ: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ተጨማሪ (67)