+ -

عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«نِعْمَتَانِ مَغْبُونٌ فِيهِمَا كَثِيرٌ مِنَ النَّاسِ: الصِّحَّةُ وَالفَرَاغُ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6412]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"አብዛኛው ሰው በነርሱ የከሰረባቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: ጤንነትና ነፃ (ትርፍ) ወቅት"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6412]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ በሰዎች ላይ ከዋላቸው ፀጋዎች መካከል አብዛኛው ሰው ያለ አግባብ በመጠቀም ስለሚከስርባቸው ሁለት ትላልቅ ፀጋዎች ተናገሩ። የሰው ልጅ የጤንነት ፀጋ ነፃ (ከትርፍ) ጊዜ ጋር አብሮ ሲሰበሰቡለት አብዛኛውን ጊዜ ከአምልኮ ሲሳነፍ ነው የሚገኘው። ይህ ክስረት ነው። የአብዛኛው ሰው ሁኔታም እንዲሁ ነው። ትርፍ ወቅቱንና ጤንነቱን አላህን በማምለክ ከተጠቀመበት ግን ዱንያ የመጪው አለም መዝሪያ ናትና ትርፋማ ይሆናል። ዱንያ ውስጥ ትርፉ በመጪው አለም የሚገኝበት ንግድ አለ። ትርፍ ወቅት ከጊዜ በኋላ መጠመድ ይከተለዋል። ጤንነትም በሽታ ይከተለዋል። ሌላው ቀርቶ እርጅና ብቻ እንኳ መምጣቱ በቂ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በሐዲሡ ውስጥ ኋላፊነት ያለበት ሰው እንደ ነጋዴ ሲመሰል ጤንነትና ትርፍ ጊዜ ደግሞ እንደ ካፒታል ተመስለዋል። ካፒታሉን አሳምሮ የተጠቀመ ሰው ትርፍ ሲያገኝ ያባከነው ደግሞ ይከስራልም ይፀፀታልም።
  2. ኢብኑ ኻዚን እንዲህ ብለዋል: "ፀጋ ማለት ሰው የሚጣቀምበትና የሚደሰትበት ነገር ነው። ኪሳራ ማለት አንድን ነገር በእጥፍ ዋጋው መግዛት ወይም ከሚገባው ዋጋ ባነሰ መሸጥ ማለት ነው። ሰውነቱ ጤነኛ ሆኖና ቆልፈው ከሚይዙት ወጥመዶችም ነፃ ሆኖ ከዚያም ለመጪው አለም ጥቅሙ ያልለፋ ሰው በንግዱ አለም እንደከሰረ ነው የሚቆጠረው።"
  3. ጊዜያቸው ከማለፉ በፊት ወደ አላህ ለመቃረብና መልካም ለመስራት ጤንነትንና ትርፍ ጊዜን መጠቀም ላይ ጉጉት ሊኖረን እንደሚገባ እንረዳለን።
  4. የአላህን ፀጋ ማመስገን አላህን በመገዛት ላይ በማዋል ነው የሚሆነው።
  5. ቃዲ አቡበከር ቢን አልዐረቢ እንዲህ ብለዋል: «አላህ ለባሮቹ በዋለው የመጀመሪያ ደረጃ ፀጋ ዙሪያ ዑለማዎች የተለያየ ሀሳብ ሰጥተዋል: "ኢማን" ተብሏል፤ "ህይወት" ተብሏል፤ "ጤንነት" ተብሏል፤ የመጀመሪያው አጠቃላዩ ፀጋ ስለሆነ የተሻለውም እርሱ ነው። ህይወትና ጤንነት አለማዊ ፀጋዎች ናቸው። እነዚህ ነገሮች ከኢማን ጋር እስካልተቆራኙ ድረስም ትክክለኛ ፀጋ አይሆኑም። አብዛኛው ሰው እነዚህ ሶስቱም ሲሰጠው ይከስርበታል። ማለትም ትርፉን ያስወግዳል ወይም ይቀንሳል። እረፍት ላይ ከምታዘወትረውና በመጥፎ ከምታዘው ነፍሱ ጋር አብሮ በመቀጠል የአላህን ህጎች ከመጠበቅና አምልኮ ላይ ከመዘውተር የተወ ሰው በርግጥም ከስሯል። ልክ እንደዚሁ ትርፍ (ነፃ) ወቅት ኑሮት ያልተጠቀመበትም ከስሯል። የተጠመደ ሰው ትርፍ (ነፃ) ወቅት ካለው ሰው የተለየ ምክንያት ይኖረዋል። ትርፍ ወቅት ያለው ምክንያት ስለማይኖረው ተጠያቂነት ይጠብቀዋል።»