عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ رضي الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«مَنْ أَكَلَ ثُومًا أَوْ بَصَلًا، فَلْيَعْتَزِلْنَا -أَوْ قَالَ: فَلْيَعْتَزِلْ- مَسْجِدَنَا، وَلْيَقْعُدْ فِي بَيْتِهِ»، وَأَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أُتِيَ بِقِدْرٍ فِيهِ خَضِرَاتٌ مِنْ بُقُولٍ، فَوَجَدَ لَهَا رِيحًا، فَسَأَلَ فَأُخْبِرَ بِمَا فِيهَا مِنَ البُقُولِ، فَقَالَ قَرِّبُوهَا إِلَى بَعْضِ أَصْحَابِهِ كَانَ مَعَهُ، فَلَمَّا رَآهُ كَرِهَ أَكْلَهَا، قَالَ: «كُلْ فَإِنِّي أُنَاجِي مَنْ لاَ تُنَاجِي».
ولِمُسْلِمٍ عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللهِ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: «مَنْ أَكَلَ مِنْ هَذِهِ الْبَقْلَةِ، الثُّومِ - وقَالَ مَرَّةً: مَنْ أَكَلَ الْبَصَلَ وَالثُّومَ وَالْكُرَّاثَ فَلَا يَقْرَبَنَّ مَسْجِدَنَا، فَإِنَّ الْمَلَائِكَةَ تَتَأَذَّى مِمَّا يَتَأَذَّى مِنْهُ بَنُو آدَمَ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 855]
المزيــد ...
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
«"ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት የበላ ሰው ከኛ ገለል ይበል ወይም ከመስጂዳችን ገለል ይበል። ቤቱም ይቀመጥ" አሉ። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አረንጓዴ አታክልት ያለበት ድስት መጣላቸው። ውስጡም የሆነ ጠረን ሸተታቸው። ሲጠይቁም ውስጡ ስላለው ቡቃያ ተነገራቸው። እርሳቸውም ከርሳቸው ጋር ወደነበረ አንድ ባልደረባቸው "አስጠጉት" አሉ። እሳቸው መብላቱን እንደጠሉ ሰውየው መመልከቱን ባስተዋሉ ጊዜ እርሳቸውም "ብላ እኔ አንተ የማታወራው ጋር ስለማወራ ነው።" አሉት።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 855]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት የበላ ሰው የጀማዓ ሶላት የሚገኙ ወንድሞቹን በጠረኑ እንዳያውክ መስጂድ ከመምጣት ከለከሉት። ይህ መስጂድ ከመምጣት የመጣው ክልከላ ግን የውግዘት ክልከላ ነው። መብላቱ የሚፈቀድ ምግብ ስለሆነ ክልከላው ከመብላት አይደለም። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አረንጓዴ አትክልት ያለበት ድስት መጣላቸው። ከድስቱ ውስጥም ጠረንን ባሸተቱ ጊዜና ውስጡ ያለው ነገር ምንነቱ ሲነገራቸው ከመብላት ተቆጥበው አንዱ ባልደረባቸው እንዲበላ አቀረቡለት። ሰውዬውም እርሳቸውን ተከትሎ መብላቱን ጠላ። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሰውዬውን የተመለከቱት ጊዜ እንዲህ አሉት: "ብላ! እኔ ያልበላሁት በራእይ ከመላእክት ጋር ስለምንሾካሾክ ነው።"
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሰው ልጆች በመጥፎ ሽታ እንደሚታወኩት መላእክትም ይታወካሉ በማለት ተናገሩ።