+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَوْلَا أَنْ أَشُقَّ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ -أَوْ: عَلَى أُمَّتِي- لَأَمَرْتُهُمْ بِالسِّوَاكِ عِنْدَ كُلِّ صَلَاةٍ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 252]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"በአማኞች ላይ ወይም በኡመቴ ላይ እንዳይከብዳቸው ብዬ ነው እንጂ በሁሉም ሶላቶች ወቅት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 252]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከኡመታቸው መካከል አማኞች ለሆኑት እንዳይከብድባቸው ባይሰጉላቸው ኖሮ ከሁሉም ሶላቶች ጋር መፋቂያን መጠቀም ግዴታ ያደርጉት እንደነበር ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኡመታቸው ላይ ያላቸው እዝነትና እንዳይከብድባቸውም የሚጠነቀቁላቸው መሆናቸውን እንረዳለን።
  2. የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትእዛዝ ሱና መሆኑን የሚጠቁም ማስረጃ እስካልመጣ ድረስ በመሰረቱ ግዴታ ነው።
  3. ሁሉም ሶላት ዘንድ የመፋቅን ተወዳጅነትና ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
  4. ኢብኑ ደቂቅ አልዒድ እንዲህ ብለዋል: «ወደ ሶላት በሚቆም ወቅት መፋቅ የተወደደበት ጥበብ ሶላት ወደ አላህ መቃረቢያ ወቅት ስለሆነ ነው። ይህ ደሞ አምልኮውን ማላቅህን ለማንፀባረቅ ሲባል የተሟላ ሁኔታንና ንፁህ መሆንን ይጠይቃል።»
  5. የሐዲሡ ጥቅል ሀሳብ ፆመኛ እንኳን ቢሆን ፀሃይ ዘንበል ካለች በኋላም መፋቁ እንደሚወደድለት ያካትታል። (ፆመኛ ሁኖ) በዙህርና ዐስር ሶላት ወቅት መፋቅን ይመስል።