+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَا تَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ حَتَّى تُؤْمِنُوا، وَلَا تُؤْمِنُوا حَتَّى تَحَابُّوا، أَوَلَا أَدُلُّكُمْ عَلَى شَيْءٍ إِذَا فَعَلْتُمُوهُ تَحَابَبْتُمْ؟ أَفْشُوا السَّلَامَ بَيْنَكُمْ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 54]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
'እስክታምኑ ድረስ ጀነት አትገቡም። እስክትዋደዱ ድረስም አታምኑም። የፈፀማችሁት ጊዜ የምትዋደዱበትን አንዳች ነገር ልጠቁማችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አሰራጩ።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 54]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአማኞች በስተቀር ማንም ጀነት እንደማይገባ፤ ከፊሉ ከፊሉን እስኪወድ ድረስም ኢማን እንደማይሞላና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሁኔታም እነደማይስተካከል ገለፁ። ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በርሱ አማካኝነት ውዴታ የሚዳረስበትን በላጭ ነገር ጠቆሙ። እርሱም: በሙስሊሞች መካከል አላህ ለባሮቹ ሰላምታ መለዋወጫ ያደረገውን ሰላምታን ማሰራጨት ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በእምነት ካልሆነ በቀር ጀነት መግባት እንደሌለ እንረዳለን።
  2. የትኛውም ሙስሊም ለነፍሱ የሚወደውን ለወንድሙ መውደዱ ከኢማን መሟላት መገለጫዎች መካከል አንዱ ነው።
  3. ለሙስሊሞች ሰላምታን ማብዛትና መለዋወጥ በሰዎች መካከል ውዴታንና ደህንነትን ስለሚያሰራጭ ይወደዳል።
  4. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "በመካከላችሁ" ስላሉ "አሰላሙ ዓለይኩም" ከሙስሊም ጋር ካልሆነ በቀር አይባልም።
  5. ሰላምታን መለዋወጥ መቆራረጥን፣ መኮራርፍንና መጣላትን ያስወግዳል።
  6. በሙስሊሞች መካከል የመዋደድን አንገብጋቢነት እንረዳለን። እርሱም ኢማንን ከሚሞሉ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።
  7. በሌላ ሐዲሥ የተሟላው የሰላምታ ይዘት "አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ" እንደሆነ መጥቷል። "አስሰላሙ ዐለይኩም" የሚለውም በቂ ነው።