عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَنْ عَالَ جَارِيَتَيْنِ حَتَّى تَبْلُغَا جَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ أَنَا وَهُوَ» وَضَمَّ أَصَابِعَهُ.
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2631]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦
"ሁለት ሴት ልጆችን እስኪደርሱ ድረስ የተንከባከበ ሰው የትንሳኤ ቀን እኔና እሱ እንዲህ ሆነን ይመጣል።" ጣታቸውንም አጣበቁ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2631]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁለት ሴት ልጆችን ወይም እህቶችን የተለገሰና ለአቅመ ሄዋን እስኪደርሱ ድረስም ለነርሱ ቀለባቸውን፣ በመልካም ማነፁን፣ ወደ መልካም መጠቆሙን፣ ከመጥፎ መከልከሉንና የመሳሰሉትን ሀላፊነቶች እየተወጣ የተንከባከባቸው ሰው የትንሳኤ ቀን እርሱና ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንደዚ ሆነን ይመጣል ብለው መጠቆሚያ ጣታቸውንና መሀል ጣታቸውንም አጣብቀው አሳዩ።