+ -

عن ابْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما أنه سَمِعَ رَجُلًا يَقُولُ: لَا وَالْكَعْبَةِ، فَقَالَ ابْنُ عُمَرَ: لَا يُحْلَفُ بِغَيْرِ اللَّهِ، فَإِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«مَنْ حَلَفَ بِغَيْرِ اللهِ فَقَدْ كَفَرَ أَوْ أَشْرَكَ».

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وأحمد] - [سنن الترمذي: 1535]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንደተላለፈው የሆነ ሰው እንዲህ ሲል ሰሙ፡ "በካዕባ ይሁንብኝ በፍፁም!" ኢብኑ ዑመርም ረዲየሏሁ ዐንሁማ እንዲሁ አሉ፡ "ከአሏህ ውጭ ባለ አካል አይማልም! ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁና
'ከአሏህ ውጭ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አጋርቷል።'"

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 1535]

ትንታኔ

በአሏህ ወይም በስምና ባህርያቱ ካልሆነ በቀር ከዛ ውጪ በሆነ መሀላ የማለ ሰው በአላህ ክዷል ወይም አጋርቷል እያሉን ነው። ምክንያቱም በአንድ አካል መማል እሱን ማላቃችንን ያስፈርዳል፤ በእውነቱ ልቅና ደግሞ የሚገባው ለአሏህ ብቻ ነው። ስለዚህም በሱ ወይም ከስምና ባህሪዎቹ መካከል በአንዱ ካልሆነ በስተቀር አይማልም። ይህ መሀላ ከትንሹ ሽርክ የሚመደብ ነው። ይሁን እንጂ የማለው ሰው የማለበትን አካል እንደ አሏህ ወይም ከዛም በላይ አልቆት ከሆነ ግን መሃላው ትልቁ ሽርክ ይሆናል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht Azerisht الأوزبكية الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በመሀላ ማላቅ ጥራት የተገባው የአሏህ ሐቅ ነው። በመሆኑም በአላህ ፣ በስምና ባህርያቱ ካልሆነ በቀር በሌላ አይማልም።
  2. ሰሓቦች በመልካም ለማዘዝ እና ከመጥፎ ለመከልከል የነበራቸውን ጉጉት ያሳያል፤ በተለይም ጥፋቱ ሽርክን ወይም ክህደትን የሚመለከት ሲሆን የበለጠ ጉጉት አላቸው።