+ -

عَنْ ‌عَبْدِ اللهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ رضي الله عنها أَنَّهُ سَمِعَ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«إِذَا سَمِعْتُمُ الْمُؤَذِّنَ فَقُولُوا مِثْلَ مَا يَقُولُ، ثُمَّ صَلُّوا عَلَيَّ، فَإِنَّهُ مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلَاةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا، ثُمَّ سَلُوا اللهَ لِيَ الْوَسِيلَةَ، فَإِنَّهَا مَنْزِلَةٌ فِي الْجَنَّةِ، لَا تَنْبَغِي إِلَّا لِعَبْدٍ مِنْ عِبَادِ اللهِ، وَأَرْجُو أَنْ أَكُونَ أَنَا هُوَ، فَمَنْ سَأَلَ لِيَ الْوَسِيلَةَ حَلَّتْ لَهُ الشَّفَاعَةُ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 384]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፦
"ሙአዚኑን የሰማችሁ ጊዜ የሚለውን አምሳያ በሉ። ከዚያም በኔ ላይ ሶለዋት አውርዱ። እነሆ በኔ ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶለዋት ያወርድለታል። ከዚያም ለኔ ከአላህ ወሲላን ጠይቁልኝ። እርሷም ጀነት ውስጥ ያለች ደረጃ ናት። ከአላህ ባሮች መካከል ለአንድ ባሪያ እንጂ አትገባም። እርሱም እኔ እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ወሲላን ለኔ የጠየቀልኝ ሰው ለርሱ ምልጃዬ ትፀናለታለች።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 384]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት አዛን የሚያደርግን ሰው የሰማ ከ"ሐይየዐለተይን" ውጪ ከኋላው አስከትሎ (ሙአዚኑ) የሚለውን አምሳያ እንዲል ጠቆሙ። ከ"ሐይየዐለተይን" በኋላ ግን "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ" ይላል። አዛኑ ከተጠናቀቀ በኃላም በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላትን ያወርዳል። እነሆ በርሳቸው ላይ አንዲትን ሶላት ያወረደ በርሱ ምክንያት አላህ በርሱ ላይ አስር ሶላት ያወርድበታልና። አላህ በባሪያው ላይ ሶላት አወረደ ማለት መላኢኮች ዘንድ ባሪያውን ማወደሱ ነው።
ቀጥለውም ወሲላን ከአላህ ለሳቸው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንድንጠይቅ አዘዙ። እርሷም በጀነት ውስጥ የምትገኝ ከፍተኛዋ ደረጃ ናት። ይህቺ ስፍራም ከሁሉም የአላህ ባሮች መካከል ለአንድ ባሪያ እንጂ ለማንም አትሰጥም አትበጅምም (አትገባም)። ያ ባሪያ እኔ እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ መልኩ የተናገሩት ለመተናነስ ብለው ነው እንጂ ይህቺ ከፍተኛ ደረጃ ለአንድ ባሪያ እንጂ ለማንም የማትሆን ከሆነች ያ አንድ ባሪያ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንጂ ማንም አይሆንም። እሳቸው ከፍጡራን ሁሉ በላጩ ፍጡር ናቸውና።
ቀጥለው ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወሲላን ከአሏህ የለመነ ሰው የርሳቸውን ምልጃ እንደሚያገኝ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ገለፁ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الأوكرانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሙአዚንን ጥሪ በመመለስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. ለሙአዚን ከመለስን በኋላ በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ላይ ሶላት የማውረድን ትሩፋት እንረዳለን።
  3. ሶላት ካወረድንባቸው በኋላ ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወሲላን በመጠየቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  4. የወሲላ ምንነትና ጉዳዩዋ ከፍ ያለ መሆኑ መገለፁ። ለአንድ ባሪያ እንጂ አትበጅምና (አትገባም)።
  5. በዚህች ከፍተኛ ደረጃ በመነጠላቸው የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ደረጃ መገለፁ።
  6. ለነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአሏህ ወሲላን የጠየቀላቸው ሰው የርሳቸው ምልጃ ትፀድቅለታለች።
  7. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህቺ ደረጃ የርሳቸው ከመሆኗም ጋር ኡመታቸው ዱዓ እንዲያደርጉላቸው መፈለጋቸው ትህትናቸውን ይገልፃል።
  8. መልካም ስራ በአስር ማብዛቱ የአላህ ትሩፋትና እዝነት ስፋቱን ያስረዳናል።