+ -

عن عمر بن الخطاب رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«إِذَا قَالَ الْمُؤَذِّنُ: اللهُ أَكْبَرُ اللهُ أَكْبَرُ، فَقَالَ أَحَدُكُمُ: اللهُ أَكْبَرُ اللهُ أَكْبَرُ، ثُمَّ قَالَ: أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، قَالَ: أَشْهَدُ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، ثُمَّ قَالَ: أَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، قَالَ: أَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، ثُمَّ قَالَ: حَيَّ عَلَى الصَّلَاةِ، قَالَ: لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللهِ، ثُمَّ قَالَ: حَيَّ عَلَى الْفَلَاحِ، قَالَ: لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلَّا بِاللهِ، ثُمَّ قَالَ: اللهُ أَكْبَرُ اللهُ أَكْبَرُ، قَالَ: اللهُ أَكْبَرُ اللهُ أَكْبَرُ، ثُمَّ قَالَ: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، قَالَ: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ مِنْ قَلْبِهِ دَخَلَ الْجَنَّةَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 385]
المزيــد ...

ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
'አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜ አንዳችሁ ከልቡ 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤ ከዚያም አዛን ባዩ: 'አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ እመሰክራለሁ።) ያለ ጊዜም 'አሽሀዱ አንላ ኢላሃ ኢለሏህ' ካለ፤ ከዚያም አዛን ባዩ: 'አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ' (ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ።) ያለ ጊዜም 'አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ' ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ሐይየ ዐለስ-ሶላህ' (ኑ ወደ ሶላት) ባለ ጊዜም 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ' (ብልሀትም ሆነ ኃይል በአላህ ካልሆነ በቀር የለም።) ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ሐይየ ዐለል ፈላሕ' (ኑ ወደ ስኬት!) ባለ ጊዜም 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ' (ብልሀትም ሆነ ኃይል በአላህ ካልሆነ በቀር የለም።) ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) ያለ ጊዜም 'አላሁ አክበሩ አላሁ አክበር' ካለ፤ ቀጥሎ አዛን ባዩ: 'ላ ኢላሀ ኢለሏህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም።) ያለ ጊዜም 'ላ ኢላሀ ኢለሏህ' ካለ ጀነት ገባ።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 385]

ትንታኔ

አዛን ማለት የሶላት ወቅት መግባቱን ለሰዎች ማሳወቂያ ነው። የአዛን ቃላቶች የኢማንን መሰረተ ሀሳቦች የጠቀለሉ ቃላቶች ናቸው።
በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አዛን በሚሰማ ወቅት የተደነገገውን ገለፁ። እሱም አዛን ሰሚው አዛን ባዩ እንደሚለው ማለቱ ነው። አዛን ባዩ 'አላሁ አክበር' ያለ ጊዜ ሰሚውም 'አላሁ አክበር' ይላል በዚህ መልኩ አዛን ባዩ ያለውን በማለት ይቀጥላል። 'ሐይየ ዐለስ-ሶላህ' እና 'ሐይየ ዐለል ፈላሕ' በሚልበት ጊዜ ግን ሰሚው 'ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላህ ' ይበል።
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚህን ቃላቶች ከልቡ አጥርቶ ከአዛን ባዩ ጋር የመላለሰ ሰው ጀነት እንደሚገባ ገለፁ።
የአዛን ቃላቶች ትርጉም: "አላሁ አክበር" ማለት ጥራት የተገባው አላህ ከሁሉም ነገር እጅግ ታላቅና የላቀ ነው ማለት ነው።
"አሽሀዱ አንላ ኢላሀ ኢለሏህ" ማለት ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም ማለት ነው።
"አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ" ማለት ሙሐመድ አላህ የላካቸው የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውንና እሳቸውን መታዘዝም ግዴታ መሆኑን በምላሴና በልቤ እርግጠኛ ሆኜ እመሰክራለሁ ማለት ነው።
"ሐይየ ዐለስ-ሶላህ" ማለት ወደ ሶላት ኑ! ማለት ሲሆን ሰሚው የሚለው "ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ" ማለት ደግሞ የአላህን ትእዛዝ ለመተግበር ከሚከለክሉ ነገሮች ለመዳን የሚያስችል ብልሀትም፤ ለመተግበር የሚያስችል ሀይልም፤ በማንኛውም ነገር ላይም ችሎታ የለም በአላህ መግጠም ቢሆን እንጂ ማለት ነው።
"ሐይየ ዐለል ፈላሕ" ማለት ወደ ስኬት መንገድ ኑ! ማለት ነው። ስኬቱም ጀነትን ማግኘትና ከእሳት መዳን ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከሁለቱ "ሀይየዐለተይን" ("ሐይየ ዐለስ-ሶላህ" እና "ሐይየ ዐለል ፈላሕ") ውጪ የአዛን ባይን ጥሪ በሚለው አምሳያ መመለስ፤ በሁለቱ "ሐይዐለተይን" ወቅት ደግሞ "ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢላ ቢላሂ" በማለት መመለስ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።