عن قيس بن عاصم رضي الله عنه قال:
أتيتُ النبيَّ صلى الله عليه وسلم أُريدُ الإسلامَ، فأَمَرَني أن أغتَسِلَ بماءٍ وسِدرٍ.
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي] - [سنن أبي داود: 355]
المزيــد ...
ከቀይስ ቢን ዓሲም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦
"ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ እስልምናን መቀበል ፈልጌ መጣሁ። እሳቸውም በውሃና በቁርቁራ ቅጠል እንድታጠብ አዘዙኝ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ነሳኢ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 355]
ቀይስ ቢን ዓሲም ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እስልምናን መቀበል ፈልጎ መጣ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በውሃ እና ቅጠሉን ለማንፃት በሚገለገሉበትና ጥሩ መአዛ ባለው የቁርቁራ ዛፍ ቅጠል እንዲታጠብ አዘዙት።