عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضيَ اللهُ عنهُما قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«البَسُوا مِنْ ثِيَابِكُمُ البَيَاضَ، فَإِنَّهَا مِنْ خَيْرِ ثِيَابِكُمْ، وَكَفِّنُوا فِيهَا مَوْتَاكُمْ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي وابن ماجه] - [سنن الترمذي: 994]
المزيــد ...
ከኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዓንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ:
"ነጭ ልብስ ምርጡ ልብሳችሁ ነውና ከልብሶቻችሁ መካከል ነጩን ልብስን ልበሱ። ሟቾቻችሁንም በርሱ ከፍኑ።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ቲርሚዚና ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 994]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ነጭ ልብስ ምርጥ ልብስ ስለሆነ ወንዶች ነጭ ልብስ እንዲለብሱና ሟቾቻቸውንም በነጭ ልብስ እንዲከፍኑ ጠቆሙ።