عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه أَنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ:
«إِذَا مَاتَ الْإِنْسَانُ انْقَطَعَ عَنْهُ عَمَلُهُ إِلَّا مِنْ ثَلَاثَةٍ: إِلَّا مِنْ صَدَقَةٍ جَارِيَةٍ، أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ، أَوْ وَلَدٍ صَالِحٍ يَدْعُو لَهُ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1631]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"የሰው ልጅ ሲሞት ከሶስት ስራዎቹ ውጪ ስራዎቹ ከርሱ ይቋረጣሉ። ሰደቀቱል ጃሪያህ (ተሻጋሪ ምፅዋቶቹ) ወይም ጠቃሚ ዕውቀት ያስተላለፈ ወይም ለርሱ ዱዓ የሚያደርግለት መልካም ልጅ ያለው ሲቀር ሌሎቹ ስራዎቹ ይቋረጣሉ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1631]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የሞተ ሰው በመሞቱ ስራው እንደሚቋረጥ፤ ከነዚህ ሶስት ስራዎች ውጪም ከሞተ በኋላ ምንዳ የሚያገኝበት እንደሌለው ተናገሩ። ሶስቱ ስራዎች ግን ሰበባቸው እርሱ ስለሆነ አይቋረጡም።
የመጀመሪያው: እንደወቅፍ፣ መስጂድ መገንባት፣ ጉድጓድ መቆፈርና ሌሎች ምንዳቸው የማይቋረጥና የሚዘወትር ምፅዋት ናቸው።
ሁለተኛው: ጠቃሚ ዕውቀትን ያስተላለፈ፡ ዕውቀት ሰጢ መጽሐፍትን እንደመፃፍ፣ የሆነን ግለሰብ ማስቀራትና ከሞተ በኋላ ይህ የቀራው ግለሰብ እውቀቱን በማሰራጨት ላይ መሳተፍን የመሰለ ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት ነው።
ሶስተኛው: ለወላጆቹ ዱዓ የሚያደርግ አማኝ መልካም ልጅ ነው።