عن سعد بن عبادة رضي الله عنه أنه قال:
يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنَّ أُمَّ سَعْدٍ مَاتَتْ، فَأَيُّ الصَّدَقَةِ أَفْضَلُ؟، قَالَ: «الْمَاءُ»، قَالَ: فَحَفَرَ بِئْرًا، وَقَالَ: هَذِهِ لِأُمِّ سَعْدٍ.
[حسن بمجموع طرقه] - [رواه أبو داود والنسائي وابن ماجه] - [سنن أبي داود: 1681]
المزيــد ...
ከሰዕድ ቢን ዑባዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሰዕድ እናት ሞተች ማንኛው ምፅዋት ነው በላጩ? እርሳቸውም "ውሃ" አሉ። እርሱም ጉድጓድ ቆፈረና "ይህቺ ለሰዕድ እናት ነው።" አለ።»
- - [ሱነን አቡዳውድ - 1681]
የሰዕድ ቢን ዑባዳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እናት ሞተች። ለናቱ ሊመፀውት የሚችለው በላጩ የምፅዋት አይነት የትኛው እንደሆነም ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠየቃቸው። እርሳቸውም በላጩ ምፅዋት ውሃ እንደሆነ ነገሩት። እርሱም ጉድጓድ ቆፈረና ለእናቱ ምፅዋት አደረጋት።