+ -

عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَا مِنْكُمْ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا سَيُكَلِّمُهُ اللهُ، لَيْسَ بَيْنَهُ وَبَيْنَهُ تُرْجُمَانٌ، فَيَنْظُرُ أَيْمَنَ مِنْهُ فَلَا يَرَى إِلَّا مَا قَدَّمَ، وَيَنْظُرُ أَشْأَمَ مِنْهُ فَلَا يَرَى إِلَّا مَا قَدَّمَ، وَيَنْظُرُ بَيْنَ يَدَيْهِ فَلَا يَرَى إِلَّا النَّارَ تِلْقَاءَ وَجْهِهِ، فَاتَّقُوا النَّارَ وَلَوْ بِشِقِّ تَمْرَةٍ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1016]
المزيــد ...

ከዓዲይ ቢን ሓቲም (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ከናንተ መካከል በርሱና በአላህ መካከል አስተርጓሚ ሳይኖር አላህ የሚያናግረው ቢሆን እንጂ አንድም ሰው የለም ወደ ቀኝ ይመለከታል። ያሳለፈውን እንጂ ሌላ ምንም አይመለከትም። ወደ ግራም ይመለከታል ካሳለፈው በቀር ሌላ ምንም አይመለከትም። ከፊትለፊቱ ይመለከታል በፊትለፊቱ ከእሳት ውጭ ሌላ ምንም አይመለከትም። በተምር ክፋይ እንኳ ቢሆን እሳትን ተጠንቀቁ።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1016]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁሉም አማኝ የትንሳኤ ቀን ብቻውን አላህ ፊት እንደሚቆምና አላህም ማንም በመካከላቸው ንግግሩን የሚተረጉም አስተርጓሚ ሳይኖር እንደሚያናግረው ተናገሩ። ከፊት ለፊቱ ካለችው እሳት ለመዳን የሚሄድበት መንገድ ያገኝ እንደሁ በሚል በድንጋጤ ብዛት ወደ ግራና ቀኝ አቅጣጫ እንደሚመለከትም ተናገሩ። ወደ ቀኝ አቅጣጫ ሲመለከትም ካሳለፈው መልካም ስራ በቀር ሌላ ምንም አይመለከትም። ወደ ግራ አቅጣጫ ሲመለከትም ካሳለፈው መጥፎ ስራ በቀር ሌላ ምንም አይመለከትም። ከፊትለፊቱ ሲመለከትም ከእሳት በቀር ሌላ ምንም አይመለከትም። በሲራጥ ላይ ማለፍ የግዱ ስለሆነበት እሳትን ወደ ጎን አድርጎ መተውም አልተቻለውም። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተምር ክፋይን የምታህል ትንሽ ነገር እንኳ በመመፅወት በናንተና በእሳት መካከል የሚከልል የመልካም ስራና የምፅዋት ጋሻ አዘጋጁ አሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ብታንስ እንኳ ምፅዋት በመስጠት ላይ፣ ምስጉን ባህሪያትን በመላበስ ላይ፣ ንግግርን አለስልሶ በመኗኗር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. የፍርዱ ቀን አላህ ወደ ባሮቹ በመካከላቸው ግርዶሽ፣ አማካኝና አስተርጓሚ ሳይኖር የሚቀርብ መሆኑን እንረዳለን። ስለዚህም የትኛውም አማኝ የጌታውን ትእዛዝ ከመቃረን መጠንቀቅ ይገባዋል።
  3. አንድ ሰው የሚመፀውተው ነገር ትንሽ እንኳ ብትሆን ከእሳት መጠበቂያው ልትሆን ስለምትችል ሊያሳንሳት እንደማይገባው እንረዳለን።
ተጨማሪ