+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«قَالَ اللهُ: أَنْفِقْ يَا ابْنَ آدَمَ أُنْفِقْ عَلَيْكَ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5352]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ እንዲህ ብሏል 'የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ላንተም ይሰጥሃል!'"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5352]

ትንታኔ

ከፍ ያለውና የላቀው አላህ "የአደም ልጅ ሆይ! ግዴታም ይሁን ተወዳጅ የሆኑብህን ወጪዎች ለግስ! ላንተም ሲሳይን አሰፋልሃለሁ፣ ያዋጣኸውን ወጪ ልውጫ እሰጥሃለሁ፣ በሰጠሁህም ነገር ላንተ እባርክልሃለሁ" ማለቱን ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በአላህ መንገድ መስጠትና መመፅወት መበረታታቱን እንረዳለን።
  2. መልካም በሆኑ መንገዶች ላይ ወጪ ማድረግ ሲሳያችን በረከት እንዲያገኝና እንዲባዛ ከሚያደርጉ እንዲሁም ሰውዬው ያወጣውን ወጪ አላህ እንዲተካለት ከሚያደርጉ ትልልቅ ምክንያቶች መካከል ነው።
  3. ይህ ሐዲሥ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከጌታቸው ከሚያስተላልፉት ሐዲሥ መካከል አንዱ ነው። ሐዲሠል ቁድሲይ ወይም ሐዲሠል ኢላሂይ በመባል ይጠራል። ቃሉም ሀሳቡም ከአላህ ሲሆን ነገር ግን ቁርአን ከሌሎች የተለየበት የሆኑ በማንበቡ (በየፊደላቱ ሐሰና የሚያስገኘውን) አምልኮን መፈፀም፣ እሱን ለማንበብ ውዱእ ማድረግና አምሳያውን ማንም እንደማያመጣ መነገሩ፣ ተአምራዊነቱና ከዚህም ውጪ ያሉ የቁርአን መለዮዎችን አልያዘም።
ተጨማሪ