عَنْ أَبِي ذَرٍّ رضي الله عنه:
أَنَّ نَاسًا مِنْ أَصْحَابِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالُوا لِلنَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: يَا رَسُولَ اللهِ، ذَهَبَ أَهْلُ الدُّثُورِ بِالْأُجُورِ، يُصَلُّونَ كَمَا نُصَلِّي، وَيَصُومُونَ كَمَا نَصُومُ، وَيَتَصَدَّقُونَ بِفُضُولِ أَمْوَالِهِمْ، قَالَ: «أَوَلَيْسَ قَدْ جَعَلَ اللهُ لَكُمْ مَا تَصَّدَّقُونَ؟ إِنَّ بِكُلِّ تَسْبِيحَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَكْبِيرَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَحْمِيدَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَهْلِيلَةٍ صَدَقَةً، وَأَمْرٌ بِالْمَعْرُوفِ صَدَقَةٌ، وَنَهْيٌ عَنْ مُنْكَرٍ صَدَقَةٌ، وَفِي بُضْعِ أَحَدِكُمْ صَدَقَةٌ»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، أَيَأتِي أَحَدُنَا شَهْوَتَهُ وَيَكُونُ لَهُ فِيهَا أَجْرٌ؟ قَالَ: «أَرَأَيْتُمْ لَوْ وَضَعَهَا فِي حَرَامٍ أَكَانَ عَلَيْهِ فِيهَا وِزْرٌ؟ فَكَذَلِكَ إِذَا وَضَعَهَا فِي الْحَلَالِ كَانَ لَهُ أَجْرٌ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1006]
المزيــد ...
ከአቡ ዘር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
«ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረቦች መካከል የተወሰኑት ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የሀብት ባለቤቶች በምንዳ ጥለውን ሄዱ። እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ፤ እንደምንጾመው ይጾማሉ፤ በትርፍ ገንዘቦቻቸው ይመፀውታሉ።" እርሳቸውም "አላህ ለናንተ የምትመፀውቱበትን ነገር አላደረገላችሁምን? ሁሉም ተስቢሕ (ሱብሓነሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተክቢር (አላሁ አክበር) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተህሊል (ላኢላሃ ኢለሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከባሌቤታችሁ ጋር ግንኙነት በመፈፀማችሁ ሶደቃ ይገኛል።" አሉ። ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን ስሜቱን ስላበረደ በርሷ ምንዳ ይኖረዋልን?" አሉ። እርሳቸውም "እስኪ ንገሩኝ ብልቱን ሐራም ላይ ቢያኖራት ኖሮ ወንጀል አይኖርበትም ነበርን? ልክ እንደዚሁ የተፈቀደችለት ባለቤቱ ላይ ያኖራት ጊዜም ለርሱ ምንዳ ይኖረዋል።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1006]
አንዳንድ ድሃ ሶሐቦች ያሉበትን ሁኔታና ድህነታቸውን፣ ብዙ ገንዘብ ያላቸው ወንድሞቻቸው ሶደቃ በመስጠት ብዙ ምንዳ እንዳገኙት እነርሱ ግን በድህነታቸው ምክንያት ይህን ብዙ ምንዳ ለማግኘት ሶደቃ መስጠት እንዳልቻሉና እንደነርሱ ብዙ መልካም ምንዳ የሚያገኙበትን መፍትሄ ፍለጋ ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስሞታ አቀረቡ፡ ሀብታሞቹ እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ፤ እንደምንጾመውም ይጾማሉ፤ ሀብታሞች በትርፍ ገንዘቦቻቸው ምፅዋት ሲሰጡ እኛ ግን ምፅዋት አንሰጥም። ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሊያደርጉት የሚችሉትን ሶደቃ በመጠቆም እንዲህ አሏቸው: "በራሳቹ ላይ የምትመፀውቱትን ነገር አላህ አላደረገላችሁምን? (ሱብሓነሏህ/ ጥራት ለአላህ የተገባው ነው) በማለታችሁ ለናንተ የሶደቃ ምንዳ ያስገኝላችኋል፤ ልክ እንደዚሁ (አሏሁ አክበር/ አላህ ታላቅ ነው) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ (አልሐምዱሊላህ/ ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነው) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ (ላኢላሃ ኢለሏህ/ ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) ማለታችሁም ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከዚህም በላይ ሚስታችሁን መገናኘታችሁ ራሱ ሶደቃ ነው።" ሶሐቦችም ተገርመው "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን ስሜቱን ስላስደሰተ በርሷ ምንዳ ይኖረዋልን?" አሉ። እርሳቸውም "ንገሩኝ እስኪ ብልቱን ዝሙት ላይ ወይም ከዛ ውጪ በሆነ ክልክል ቦታ ላይ ቢያኖራት በርሱ ላይ ወንጀለኝነት አይኖርበትምን? ልክ እንደዚሁ የሚፈቀድለት ቦታ ላይ ካኖራት ደሞ ምንዳ ይኖረዋል።" አሉ።