+ -

عَنْ أَبي مَسْعُودٍ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِنَّ مِمَّا أَدْرَكَ النَّاسُ مِنْ كَلاَمِ النُّبُوَّةِ الأُولَى: إِذَا لَمْ تَسْتَحْيِ فَاصْنَعْ مَا شِئْتَ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6120]
المزيــد ...

ከአቢ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ሰዎች ከቀደምት ነቢያት ካገኟቸው ቃላት መካከል ካላፈርክ የፈለግከውን ስራ! የሚለው አንዱ ነው።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6120]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደዚህ ኡመት መጀመሪያ እስኪደርስ ድረስ ከቀደምት ነቢያት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወራረሱትና በመካከላቸው ሲቀባበሉት ከነበሩ አደራዎች መካከል ልትሰራው የምትፈልገውን ስራ ተመልከት! ማድረጉ የማያሳፍር ስራ ከሆነ ስራው! የሚያሳፍር ስራ ከሆነ ተወው! የሚለው ይገኝበታል። ፀያፍን ከመስራት የሚከለክለው ሀፍረት ነው። ሀፍረት የሌለው ሰው በየትኛውም ፀያፍና ውግዝ ተግባር ውስጥ ይዘፈቃል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሀፍረት የመልካም ስነ ምግባር መሰረት ነው።
  2. ሀፍረት ከነቢያት (ዐለይሂሙ ሰላም) ባህሪያት መካከል አንዱ ባህሪና ከነርሱ የተወሰደ መገለጫ ነው።
  3. ሙስሊም የሆነን ሰው የሚያስውበውንና የሚያስጌጠውን እንዲሰራ፣ የሚያቆሽሸውና የሚያጎድፈውን ደሞ እንዲተው የሚያደርገው ሀፍረት ነው።
  4. ነወዊ እንዲህ ብለዋል: «ትእዛዙ መፍቀድንም ያቀፈ ነው: ማለትም አንዳች ነገር ለመስራት ብትፈልግ ብትሰራው ከአላህም ሆነ ከሰው የማያሳፍር ከሆነ ስራ! ያለበለዚያ አትስራው ማለት ነው። የእስልምና መሽከርከሪያ ዛቢያም ይኸው ነው። የዚህም ማብራሪያ በግዴታም ይሁን በፍቃደኝነት የመጡ ትእዛዛትን መተዉ የሚያሳፍር ነው። ሐራም ተደርገውም ይሁን ተጠልተው የተከለከሉ ክልከላዎችን ደግሞ ሊሰሩ የሚያሳፍሩ ናቸው። የተፈቀዱ ነገሮች ከሆኑ ግን ለመስራት የሚያሳፍሩም አሉ፤ ለመተው የሚያሳፍሩም አሉ። ስለዚህ ይህ ሐዲሥ አምስቱን ህግጋት አካትቷል ማለት ነው። ይህ ትእዛዝ ለዛቻ ነው የመጣው ያሉም አሉ። ማለትም: ሀፍረትክ ከተነሳ የፈለግከውን ስራ አላህ በስራህ ይመነዳሀልና።
  5. ማስጠንቀቅ የተፈለገበት አነጋገር ነው ያሉም አሉ። ማለትም የማያፍር ሰው የፈለገውን ይሰራል።