عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا أَنَّهُ سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، يَقُولُ عَامَ الفَتْحِ وَهُوَ بِمَكَّةَ:
«إِنَّ اللَّهَ وَرَسُولَهُ حَرَّمَ بَيْعَ الخَمْرِ، وَالمَيْتَةِ وَالخِنْزِيرِ وَالأَصْنَامِ»، فَقِيلَ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَرَأَيْتَ شُحُومَ المَيْتَةِ، فَإِنَّهَا يُطْلَى بِهَا السُّفُنُ، وَيُدْهَنُ بِهَا الجُلُودُ، وَيَسْتَصْبِحُ بِهَا النَّاسُ؟ فَقَالَ: «لاَ، هُوَ حَرَامٌ»، ثُمَّ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عِنْدَ ذَلِكَ: «قَاتَلَ اللَّهُ اليَهُودَ إِنَّ اللَّهَ لَمَّا حَرَّمَ شُحُومَهَا جَمَلُوهُ، ثُمَّ بَاعُوهُ، فَأَكَلُوا ثَمَنَهُ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 2236]
المزيــد ...
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እርሱ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ የተከፈተ ቀን መካ ውስጥ እንዲህ ሲሉ ሰማቸው:
"አላህና መልክተኛው አስካሪ መጠጥን፣ በክትን፣ አሳማንና ጣዖታትን ከመሸጥ ከልክለዋል።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የበክት ሞራን በርሱ ጀልባዎቻችን ይለቀለቃሉ፣ ቆዳችንን እንቀባበታለን፣ ሰዎች በርሱ መብራትን በመስራት ይጠቀማሉ። ንገሩን እርሱም ክልክል ነውን?" ተባሉ። እርሳቸውም "በፍፁም እርሱም ክልክል ነው።" አሉና ቀጥለውም የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በዚህ ጊዜ እንዲህ አሉ "አላህ የሁዶችን ረገመ። አላህ ሞራን ከመጠቀም የከለከላቸው ጊዜ አሳምረው ሸጡትና የሸጡበትን ዋጋ በሉት።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 2236]
ጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መካ በተከፈተበት ዓመት መካ ሳሉ እንዲህ ሲሉ ሰማቸው "አላህና መልክተኛው አስካሪ መጠጥን፣ በክትን፣ አሳማንና ጣዖታትን ከመሸጥ ከልክለዋል።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የበክት ሞራ መሸጥ ይፈቀድልናልን? ምክንያቱም በርሱ ጀልባዎቻችንን ይጠገኑበታል፣ ቆዳዎቻችንን እንቀባለን፣ ሰዎች በርሱ ኩራዞቻቸውን ያበሩበታል።" ተባሉ። እርሳቸውም "በፍፁም እርሱን መሸጥም ክልክል ነው።" አሉና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀጠል አድርገው እንዲህም አሉ: "አላህ አይሁዶችን ይርገማቸው ያጠፋቸውና አላህ በነርሱ ላይ የእንስሳ ሞራን የከለከለ ጊዜ አቅልጠው ቅባቱን ሸጡትና ዋጋውን በሉት።"